በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መንግሥት አማራ ክልል ውስጥ ኢንቨስተሮችን እንደሚያግዝ አስታወቀ


መንግሥት አማራ ክልል ውስጥ ኢንቨስተሮችን እንደሚያግዝ አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:51 0:00

መንግሥት አማራ ክልል ውስጥ ኢንቨስተሮችን እንደሚያግዝ አስታወቀ

በህወሓት ኃይሎች የንብረት ጉዳትና ዘረፋ ተፈጽሞብናል ያሉ ኢንቨስተሮች ከጉዳታቸው አገግመው ወደ ስራ እንዲመለሱ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲደርግላቸው ጠየቁ፡፡

የህወሓት ኃይሎች ዘልቀው “ገብተውባቸዋል” በተባሉና ዘረፋ እና ውድመት አድረሰዋል በሚባሉበት የአማራ ምስራቃዊ አካባቢ 541 ከባድ፣ መካከለኛ እና ቀላል ኢንዱስትሪዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው የክልሉ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ቢሮ አስታውቋል፡፡

ከትናንት በስቲያ በደሴ ከተማ ንብረታቸው ጉዳት ከደረሰበት ባለሃብቶች፣ አገልግሎት ሰጭ ዘርፍ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ጋር በተደረገ የምክክር መድረክ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፍለ ባስተላለፉት መልእክት የወደሙትን ኃብቶች መልሶ መተካት ሳይሆን ከነበረው በተሻለ እንዲቀጥሉ የማድረግ መንግስታዊ አቅጣጫ መቀመጡንም አያይዘው ጠቁመዋል፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር መላኩ አለበል በበኩላቸው ጉዳት የደረሰባቸው ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም ጥናቶች እየተካሄዱ ነው ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG