ደሴ —
የህወሓት ኃይሎች በአፋር አብአላ በኩል በከፈቱት ወታደራዊ ጥቃት ምክንያት ከ220 ሽህ በላይ ኗሪዎች ከቀያቸው ለመፈናቀል መገደዳቸውን የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አስታወቀ፡፡
የክልሉ መንግሥት ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የህወሓት ኃይሎች ወደ አፋር ክልል እስከ 150 ኪ.ሜ ዘልቀው ገብተዋል፡፡
ሰላማዊ ሰዎች ተጥልለውባቸው የሚገኙ የጤናና የትምህርት ተቋማት ከህወሓት ኃይሎች በሚሰነዘር የከባድ መሳሪያ ጥቃት ጉዳት እንደደረሰባቸውም አመልክቷል፡፡
ህወሓት በበኩሉ ትናንት አወጣው በተባለው መግለጫ የአፋርና የትግራይ ሕዝቦች ወንድማዊ ግንኙነት ላይ ሥጋት ናቸው ባላቸው በአፋር ክልል ፕሬዚዳንት ልዩ ፖሊስና በኤርትራ መንግሥት ይደገፋል ባለው፤ "የቀይ ባህር አፋር ኃይል" ላይ ጥቃት መክፈቱን አምኗል፡፡
ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።