በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አላባማ በሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ተኩስ የከፈተ አጥቂ ሁለት ሰዎች ገደለ


አላባማ በሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ተኩስ የከፈተ አጥቂ ሁለት ሰዎች ገደለ
አላባማ በሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ተኩስ የከፈተ አጥቂ ሁለት ሰዎች ገደለ

ደቡባዊ ዩናይትድ ስቴትስ በምትገኘው በአላባማ ክፍለ ሀገር ጥቂት ሰዎች በተሰባሰቡበት ቤተ ክርስቲያን ታጣቂ ተኩስ ከፍቶ ሁለት ሰዎች ሲገድል አንድ ሌላ ሰው አቆሰለ።

ባለሥልጣናት በርሚንግሃም ከተማ አቅራቢያ በሚገኝ ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ጥቃቱን በማድረስ የተጠረጠረው ማንነቱ ያልታወቀ ሰው ተይዟል ብለዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ሰሞኑን የመሳሪያ ጥቃት በተከታታይ መድረሱ የመሳሪያ ቁጥጥር ለውጥ እርምጃን አስፈላጊነት የሚመለከተውን ክርክር ቀስቅሶታል።

ባለፈው ወር ኒው ዮርክ ባፈሎ ከተማ ውስጥ በሚገኝ የምግብ እና ሸቀጣ ሸቀጥ መደብር በዘረኛ ጥቃት አስር ጥቁር አሜሪካውያን ተገድለዋል። ከዚያም ወዲህ ቴክሳስ ዩቫልዴ ከተማ ትምህርት ቤት ውስጥ ተኩስ የከፈተ አጥቂ አስራ ዘጠኝ ተማሪዎች ጨመሮ ሃያ አንድ ሰዎች ገድሏል።

ቅዳሜ ዕለት በመዲናዋ በዋሽንግተን ትዕይንተ ህዝብ ያደረጉ በሺዎች የተቆጠሩ ሰዎች ጠበቅ ያለ የመሳሪያ ቁጥጥር ህግ እንዲደነገግ ጠይቀዋል።

XS
SM
MD
LG