በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ ህብረት መፈንቅለ መንግሥት የተደረገባት ጊኒን አገደ


ጊኒ-ኮናክሪ
ጊኒ-ኮናክሪ

የአፍሪካ ህብረት የምዕራባዊቷ አፍሪካ ጊኒን በቅርቡ በአገሪቱ በቅርቡ በተደረገው መፈንቅለ መንግሥት የቀድሞ ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴ መታሰራቸውን ተከትሎ ከህብረቱ ያገዳት መሆኑን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

የፓን አፍሪካ አካል የሆነው ህብረቱ ባወጣው የትዊተር መልዕክቱ “የጊኒ ሪፐብሊክን ከሁሉም የአፍሪካ ህብረት እንቅስቃሴዎችና ውሳኔ ሰጭ አካላት እንድትታገድ ተወሰኗል” ብሏል፡፡

ውሳኔው የመጣው በቅርቡ የጊኒ ልዩ ወታደራዊ ኃይሎች በአምባገንነት እየተከሰሱ የነበሩትን የአገሪቱን የቀድሞ ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴን በመገልበጥ ሥልጣን ከያዙ በኋላ ነው፡፡

ህብረቱ ወታደራዊ ባለሥልጣናቱ አውግዞ በአገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ ሥልጣን የያዙትን ፕሬዚዳንት ኮንዴ በአስቸኳይ እንዲለቀቁም ጠይቋል፡፡

XS
SM
MD
LG