ዋሽንግተን ዲሲ —
የአፍሪካ ህብረት በቅርቡ በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት የተወገዱባት ቡርኪና ፋሶን ከህብረቱ እንቅስቃሴዎች ማገዱን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡
የህብረቱ የፖለቲካ የሰለም የደህንነት መምሪያ ዛሬ ባወጣው የትዊት መልዕክት በአገሪቱ ህገ መንግሥታዊ ስርዓት በቦታው እስኪመለስ ድረስ ቡርኪና ፋሶን ከሁሉም የህብረት እንቅስቃሴዎች ያገዳት መሆኑን አስታውቋል፡፡
በቡርኪና ፋሶ ወታደራዊ መፈንቅለ መግሥቱ የተካሄደ ባለፈው ሳምንት መሆኑን ተመልክቷል።