በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩሲያው የዩክሬን ወረራ በአፍሪካ የምግብ እጥረትን ያባብሳል


በሮም በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ተቋም የዩናይትድ ስቴትስ ተወካይ የሆኑት ሲንዲ መኬይን በኬኒያ የካኩማ የስደተኞች የመጠለያ ጣቢያ በዩኤስኤአይዲ የተለገሱ የእርዳታ እቃዎች ሲጎበኙ፤ እአአ መጋቢት 17/2022 ቱርካና ካውንቲ፣ ኬንያ
በሮም በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ተቋም የዩናይትድ ስቴትስ ተወካይ የሆኑት ሲንዲ መኬይን በኬኒያ የካኩማ የስደተኞች የመጠለያ ጣቢያ በዩኤስኤአይዲ የተለገሱ የእርዳታ እቃዎች ሲጎበኙ፤ እአአ መጋቢት 17/2022 ቱርካና ካውንቲ፣ ኬንያ

የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታደርገውን ወረራ እስከቀጠለችበት ድረስ በርካታ የአፍሪካ አገሮች ከፍተኛ የምግብ እጥረትና የዋጋ ውድነት የሚባባስ መሆኑን አስታወቁ፡፡

አፍሪካ አብዛኛውን ስንዴና የምግብ ዘይት ከዩክሬን የምታገኝ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

ሮም በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ተቋም የዩናይትድ ስቴትስ ተወካይ የሆኑት ሲንዲ መኬይን የዓለም ትልቋ የዳቦ ቅርጫት በሆነቸው ዩክሬን ህዝብና መሬት ላይ የተቃጣው የሩሲያ ወረራ በመላው ዓለም የረሃብ አደጋን ሊደቅን ይችላል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

“የምግብና የእርሻ ድርጅት እንዳስታወቀው በሩሲያው የዩክሬን ወረራ የተነሳ በመላው ዓለም እስከ 13 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች ወደ ምግብ እጥረት ችግር ሊገፉ ይችላሉ፡፡ እውነታው የፑቲን ጦርነት ከተራቡት ላይ ወስደኝ እጀግ የጠናባቸውን እንድንመግብ የሚያስገድደን ነው፡፡ ሩሲያ የጭካኔ ጦርነቷን እስከቀጠለችበት ድረስ ንጹሃን ሰዎች ዋጋ መክፈላቸው አይቀርም፡፡”

ዩክሬን በዓመት 40 ከመቶ የሚሆነውን በቆሎና ስንዴ ወደ አፍሪካ ትልካለች፡፡

የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ ኢትዮጵያና ናይጄሪያን ጨምሮ፣ 80 አገሮች ውስጥ የሚገኙ 138 ሚሊዮን ሰዎቹን የሚመግብበትን እነዚህን ሰብሎች የሚያገኘው፣ ከአውሮፓ አገሮች መሆኑ ተገልጿል፡፡

ዓለም አቀፉ የቀይስ መስቀል ኮሚቴ 346 ሚሊዮን በላይ አፍሪካውያን የምግብ እጥረት የሚገጥማቸው ሲሆን በየቀኑ መመገብን ያቆማሉ ብሏል፡፡

ዩኒሴፍም ባወጣው መግለጫ በሚቀጥሉት ሦስት ወራት ውስጥ በአፍሪካ 11 ሚሊዮን ሰዎች ወደ ረሃብተኝነት እንድሚገፉ አስታውቋል፡፡

ያልተቋረጠው ድርቅ፣ የዝናብ እጥረትና በአንዳንድ የአፍሪካ አገሮች ያሉት ግጭቶች፣ የአፍሪካን የምግብ ችግር እንደሚያባብሱም ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG