በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ ቀውስ እና ወጣት ተኮር አፍሪካዊ መፍትሔዎች


የአፍሪካ ቀውስ እና ወጣት ተኮር አፍሪካዊ መፍትሔዎች
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:52 0:00

የአፍሪካ ቀውስ እና ወጣት ተኮር አፍሪካዊ መፍትሔዎች

የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የተመሰረተበት ቀን ግንቦት 17 ዓመታዊ መታሰቢያ የሆነውን የአፍሪካ ቀን በማስመልከት የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ባወጡት መግለጫ፣ የአፍሪካ ፈተናዎች ይበልጥ እየጨመሩ እና እየተወሳሰቡ መምጣታቸውን ገልጸዋል፡፡

የሽብርተኝነት፣ ጽንፈኛ አክራሪነት እና የድንበር ተሸጋሪ ወንጀሎችን መባባስ፤ እንዲሁም ከመልካም አስተዳደር እጦት የሚመነጩ ያሏቸው ሙስና፣ የእርስበርስ ግጭቶች እና ኢ ሕገመንግሥታዊ የሥርዓት ለውጦችን መበራከት ሊቀመንበሩ የጠቀሷቸው የአህጉሪቱ ፈተናዎች ናቸው፡፡

ከፍተኛ የወጣቶች ሥራ አጥነት እና የአህጉሪቱ ሴቶች ፈተናም አፋጣኝ ምላሽ የሚሹ ሌሎች ተግዳሮቶች እንደሆኑ አንስተዋል።፡፡ ኮቪድ 19 እና የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ደግሞ የአፍሪካን ቀውሶች ያባባሱ ክስተቶች መሆናቸውን የጠቀሱት ሙሳ ፋኪ፣ ለቀውሶቹ እልባት ለመስጠት የአፍሪካ ሕብረት የተለያዩ ተግባራትን ቢያከናውንም ውጤቱ ከፍላጎታችን ጋር አይገናኝም ብለዋል፡፡ በመሆኑም የመፍትሔ ውሳኔዎች ተግባራዊ እንዳይሆኑ የሚያደርጉ እንቅፋቶችን ማስወገድ ትኩረት ሊሰጥበት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

59ኛው የአፍሪካ ቀን በሚታሰብበት በዛሬው ዕለት፣ የሥራ አጥነትችግርን ጨምሮ በአህጉሪቱ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚመክርየፓን አፍሪካ ወጣቶች ጉባኤም በአዲስ አበባ መካሔድ የጀመረ ሲሆን፣ አብዛኛው ሕዝቧ ወጣት በሆነው አፍሪካ፣ የአሕጉሪቱን ቀውሶች ለመፍታት ወጣቶች የመሪነት ሚና ሊኖራቸው እንደሚገባ የሚገልጹት የጉባዔው ተሳታፊዎች፣ ለዚህም እድሎች ሊመቻቹ እንደሚገባ ይገልጻሉ፡፡

ከደቡብ አፍሪካ የመጣችው የጉባዔው ተሳታፊ ወጣት ሳምገለሲ ዌቹንዳ “ፈተናዎች፣ ለአህጉሪቱ እና ለወደፊትየሚጠቅም የራሳችንን መፍትሄ እንድናመነጭ እድሉን ይሰጡናል፡፡ አሁን የምንኖርበት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን፣ ቀደምቶቻችን ያቆዩልን ነው፡፡ የተሻለ ነገን ለመፍጠር ግን እኛ እድሉ አለን” ስትል ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየቷን ሰጥታለች፡፡ ለዚህ ስኬታማነት “መንግሥታት ምቹ ሁኔታዎችንሊፈጥሩ ይገባል” የምትለው ዌቹንዳ፣በጉባዔያችን የምናሳልፋቸው ውሳኔዎችም ለአህጉራችን ለውጥ ሲባል ተግባራዊ ሊሆኑ ይገባል” ስትልም አክላለች፡፡

የአስተሳሰብ ለውጥ የማምጣት የበጎ አድራጎት ተግባር ላይ ተሰማርቶ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ የጉባዔው ታዳሚ መምህር አካሉ አብርሃም ደግሞ፣ በአፍሪካ የተንሰራፋው የችግሮች መደራረብ “ወጣቱ በቁጭት ለለውጥ እንዲነሳ ሊያደርገው ይገባል” ይላል፡፡ በዚህ ሂደት ግን የአፍሪካ መንግሥታት ሕዝባቸውን መስለው በመኖር እና ችግሩ ተሰምቷቸው ትክክለኛ የመሪነት ሚናን ሊወጡ እንደሚገባ፣ ምሁራን፣ የኃይማኖት መሪዎች እና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት የየድርሻቸውን በቁርጠኝነት መወጣት እንዳለባቸው መልዕክቱን አስተላልፏፏ፡፡

አፍሪካን ለማልማት እና ለመለወጥ የሚያስፈልገው ነገር ወጣቱጋር አለ” የሚለው ላይቤሪያዊው አግዚኤም ሱፑ በበኩሉ፣

“ወጣቶች አስፈላጊው ድጋፍ ቢደረግላቸው አፍሪካ በርግጠኝነት ትቀየራለች" ይላል፡፡

በአጀንዳ 2063 እንደተመለከተው፣ “የምንፈልጋትን አፍሪካ እውን ለማድረግበርግጠኝነት ወጣቱን ነው መመልከት ያለብን፡፡ ስለዚህ የአፍሪካ መንግሥታት ወጣቱን መደገፍና ማነቃቃት አለባቸው” ሲልም አስተያቱን ያክላል፡፡

ሥራ አጥነትን ጨምሮ የአፍሪካ ችግሮችን ለመፍታት አሕጉር በቀል የሆኑየመፍትሔ አቅጣጫዎችን የመከተል አስፈላጊነት ላይ መወያየት የጉባዔው አንዱ ዓላማመሆኑን የገለጸው ደግሞ፣ የአፍሪካ ወጣቶች ልማት እና ልህቀት ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ፉአድ ገናነው፡፡

የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንም በጉባኤው መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ወጣቱ አፍሪካን ከድህነት ለማላቀቅ፣ “ከታሪክ ልምድ መውሰድ አለበት” ብለዋል፡፡

እሴቶቻችንን መጠበቅ እና ከታሪካችን መማር የወደፊቱንጊዜ በግልፅ እንድናይ ይረዳናል” ያሉት አቶ ደመቀ፣ “ቅድመ አያቶቻችን አህጉራችንን ነጻ ለማውጣት ታግለዋል፡፡

ከዚህ መስዋዕትነት ልንማር ይገባል፡፡ እናንተ አሁን ለአፍሪካ ሁለተኛ ነጻነት አስተዋጽኦ እንድታደርጉ ተጠርታችኋል፡፡ ከድህነት እና ኋላ ቀርነት ነጻ ለማውጣት” ብለዋል፡፡

ወጣቱ ለአህጉሪቱ እድገት በሚያደርገው አስተዋጽኦ ጠንካራ ድጋፍ እንደሚያስፈልገው የገለጹት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ይህን በመገንዘብ በቀጣይ የ10 ዓመት የልማት እቅዶቹ የወጣቱን ተሳትፎ ለማጉላታ ወስኖ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

XS
SM
MD
LG