በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍጋኒስታኑ ጦርነት ፍጻሜና ቀጣዩ እርምጃ


Taliban forces patrol at a runway a day after U.S. troops' withdrawal from Hamid Karzai International Airport in Kabul, Afghanistan, August 31, 2021.
Taliban forces patrol at a runway a day after U.S. troops' withdrawal from Hamid Karzai International Airport in Kabul, Afghanistan, August 31, 2021.

ዛሬ ነሀሴ 25 ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች አፍጋኒስታንን ለቀው የሚወጡበት ቀን እንደሚሆን ያስቀመጡት የመጨረሻው ቀነ ገደብ ነው፡፡ እስከዛሬ ቢያንስ 5ሺ አሜሪካውያን ዜጎችን ጨምሮ 122ሺ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮችና አጋሮቻቸው አፍጋኒስታንን ለቀው ወጥተዋል፡፡ ወደ ሥልጣን የተመለሰው ታሊባንም ዛሬ ባወጣው መግለጫ “ይህ ለወራሪዎች ትልቅ ትምህርት ነው” ብሏል፡፡ ዩናይትድ ስቴትስና የዓለም ማህበረሰብም ለታሊባን አገዛዝ እውቅና እንዲሰጥ አሳስቧል፡፡

የተባበሩት መንግሥታ የእርዳታ ድርጅቶች ግን በአፍጋኒስታን በመቆየት ሥራቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል፡፡

ረጅም ጊዜ የፈጀው ጦርነት በማብቃቱ አፍጋኒስታንን ለቀው ሲወጡ እነኚህ የመጨረሻዎቹ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች ናቸው፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንተኒ ብሊንከን

“ወታደራዊ ተልእኮው አብቅቷል፡፡ አዲሱ የዲፕሎማሲ ተልዕኮ ተጀምሯል፡፡”ብለዋል፡፡

እኤአ በ2001 በዩናይትድ ስቴትስ የተወገደው ታሊባን ዛሬ በየጎዳናው መሳሪዎችን በመተኮስ እያከበረ ባለበት ሰዓት ጀኔራል ፍራንክ መከንዚ ለቆ የመውጣቱን አጠቃላይ ሂደት እየከታተሉ ነው፡፡

ጄነራሉ ከፔንታገን ሆነው በተነካ ስሜት ሲናገሩም እንዲህ ብለዋል

“ከዚህ ለቆ የመውጣት ሂደት ጋር የተያያዙ ብዙ ልብ የሚሰብሩ ነገሮች አሉ፡፡ ልናወጣ የፈለግነውን ሁሉንም ሰው አላወጣንም፡፡”

ዩናይትድ ስቴትስ የዲሎማሲያዊ ተልዕኮ ሥራዎችዋን ወደ ኳታር አዙራለች፡፡

በአፍጋኒስታን ወደ ኋላ የቀሩትን ወደ 250 የሚሆኑትን አሜሪካውያንን እና የአፍጋን ረዳቶቻቸውን በቀጣዮቹ ቀናት ለማውጣትም ቃል ገብታለች፡፡

አንተኒ ብሊንከን እንዲህ ይላሉ

“ብዙዎቹ እስካሁን እዚያው ናቸው እነሱን ለማውጣት ያለን ቁርጠኝነት በጊዜ ገደብ አይወሰንም”

ለቆ በመውጣቱ ሂደት የሞቱትን የአፍጋኒስታን ዜጎችን ጨምሮ፣ በመውጣቱ ሂደት የደረሰው አጠቃላይ ጉዳት ግልጽ አይደለም፡፡

የአፍጋኒስታኑ ጦርነት ፍጻሜና ቀጣዩ እርምጃ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:54 0:00


ባላፈው ሳምንት ሐሙስ በደረሰው የአይሲስ የቦምብ ጥቃት ፣ 13 የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮችን ጨምሮ ከ100 መቶ በላይ የአፍጋኒስታን ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

ባለፈው እሁድ የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ፈንጂዎችን መጫኑ በተጠረጠረ አንድ የአይሲሲ ተሽከርካሪ ላይ ባደረሰው ጥቃት መኪናውና ውስጡ ያለው ፈንጅ በመቀጣጠሉ ሌሎች ተጨማሪ የአፍጋኒስታን ዜጎችም ሞተዋል፡፡

የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ጀን ሳኪ ተከታዩን ብለዋል

“13 የሠራዊት አባላትን ሞት የሰማችሁበት ቀንም ሆነ ሳምንት በፕሬዚዳንትነት ዘመናችሁ የከፋ ቀን ወይም ሳምንት ነው፡፡”

የዋይ ሀውስ ቃል አቀባይ ጄን ሳኪ ፕሬዚዳንቱ አሁንም “አፍጋኒስታንን ለቆ በመውጣቱ ውሳኔያቸው እንደጸኑ ነው” ብለዋል፡፡

በአፍጋኒስታኑ የ20 ዓመት ጦርነት ወደ 2ሺ400 የሚሆኑ የአሜሪካ ወታደሮች ሞተዋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ የአልቃይዳ መሪ ኦሳማ ቢን ላደንን የገደለች ሲሆን የአልቃይዳ አሸባሪዎች በአሜሪካ ምድር ሌላ ዳግመኛ ጥቃት እንዳያካሂዱ ማስቆም ችላለች፡፡

ይሁን እንጂ አሜሪካና አጋሮችዋ በአፍጋኒስታን ታሊባንን ማሸነፍ የሚችል መንግሥትና ሠራዊት መመስረት አልቻሉም፡፡

ብዙዎቹ አሜሪካውያን በአፍጋኒስታን እንደ ሴቶችና ልጃገረዶች ባሉ የማህረሰብ ቡድኖች የተገኙ በርካታ ድሎችና ለአሜሪካ አጋርነታቸውን የገለጹ ዜጎች ህይወት አደጋ ላይ ይወድቃል ብለው ይሰጋሉ፡፡

የዩናይትድ ስቴትስን መውጣት ተከትሎ የታሊባን ኃይሎች ዋነኛው ቃል አቀባይ ዛቢሁላ ሙሃጅድ ለአፍጋኒስታኖች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

“የዩናይትድ ስቴትስ ጦር መውጣት የሁላችንም ድል ነው” በማለት “ ይህ ለሌሎች ወራሪ ኃይሎች ትልቅ ትምህርት ነው” ብለዋል፡፡ ዩናይትድ ስቴትስና መላው ዓለም ለታሊባን አገዛዝ እውቅና እንዲሰጥም አሳስበዋል፡፡

ታሊባን ከዩናይትድ ስቴትስም ሆነ ከሌሎች ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ አባላት ጋር ጥሩ ግንኙነት መመስረት እንደሚፈልግም ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡

ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያዎችን ለህዝብ ክፍት እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል፡፡

በሌላም በኩል ዩናይትድ ስቴትስ ጦሯን ከአፍጋኒስታን ብታስወጣም የተባበሩት መንግሥታት የእርዳታ ድርጅቶች ግን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩን አፍጋኒስታዊያንን ለመርዳታ በዚያ እንደሚያቆያቸው አስታውቋል፡፡

ታሊባንን የአፍጋኒስታንን መንግሥት መቆጣጠሩን ቢያሳውቅም በመላው አገሪቱ ግን ወገ ያለው ሥርዓት ሙሉ ለሙሉ ገና አልተዘረጋም፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰአብአዊ ጉዳዮች ቢሮ አስተባባሪ ጄን ለርክ ባገሪቱ ያለው ችግርና የእርዳታ ድርጅቶች አገልግሎት በዚያ የመቆየታቸውን ነገር አስፈላጊ እንደሚያደርገው እምነታቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ዓለም አቀፉ የእርዳታ ድርጅት በግጭቱ ሳቢያ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ 3.5 ሚሊዮን ሰዎችን ጨምሮ ወደ 16 ሚሊዮን የሚሆኑን ተረጅዎችን እንደሚረዳ አስታውቋል፡፡ ይሁን እንጂ ለዚህ ከሚያስፈልገው 1.3 ቢሊዮን ውስጥ እስካሁን የተገኘው 39 ከመቶው ብቻ መሆኑንም ገልጿል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅትም ወደ አፍጋኒስታን 12.5 ቶን የሚሆን የመድሃኒት አቅርቦት መላኩን አስታውቋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፍሊፖ ግራንዴ ግን በአፍጋኒስታን ያለው ቀውስ ገና መጀመሩ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የመንግስታቱ ድርጅት አስተባባሪ የሰአብአዊ ጉዳዮች ቢሮ አስተባባሪ ጄን ለርክ “ወታደሮቹ ወጥተዋል እኛ ግን እዚህ እንቆያለን” ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG