በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአፍጋኒስታኑ ፍንዳታ ቢያንስ ሁለት ሰዎች ሞቱ



በጃላላባድ ፍንዳታው የደረሰበት ስፍራ
በጃላላባድ ፍንዳታው የደረሰበት ስፍራ

ዛሬ በአፍጋኒስታን ምስራቃዊ ክፍለ ግዛት በምትገኝ ጃላላባድ ከተማ ውስጥ በደረሱ ሶስት የቦምብ ፍንዳታዎች ቢያንስ ሁለት ሰዎች መሞታቸውና እስከ 20 የሚደርሱ መቁሰላቸውን የታሊባን ባለሥልጣናት አስታወቁ፡፡

በፍንዳታው ከተጎዱት መካከል ህጻናትና ሴቶች ይገኙበታል፡፡ ለጥቃቱ ኃላፊነቱን የወሰደ የለም፡፡

በቅርቡ ከ100 ሰዎች በላይ የሞቱበትና ካቡል አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ የደረሰውን የአጥፍቶ ማጥፋት ኃላፊነት የወሰዱት የታሊባን ተቃዋሚ የሆኑት የእስልምና መንግስት ቡድን ተዋጊዎች መሆናቸው ይታወሳል፡፡

የአሁኑ ፍንዳታ የደረሰባት ጃላላባድ የዚሁ እስላማዊ መንግሥት ቡድን ዋነኛ መናኻሪያ መሆኗም ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG