በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ “በኦሮሞ ነፃነት ታጣቂዎች” ትላንት ተፈፀመ በተባለ ጥቃት ሁለት ሰዎች ሲሞቱ አንዲት ነዋሪ መቁሰሏን ነዋሪዎችና ቤተሰቦቻቸው ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ።
የኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ ሰላም እና ጸጥታ ጽሕፈት ቤት ሁለት ሲቪል ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል ምእራብ ጉጂ ዞን ወሰን በተሻገሩ ታጣቂዎች ስለመገደላቸው አረጋግጠዋል።
የኬሌ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ሸሪፍ አደም፣ በጥይት የቆሰሉ ሁለት ሰዎች ለሕክምና ሆስፒታላቸው ገብተው እንደነበርና ለተሻለ ሕክምና ወደ ሌላ ቦታ ከተላኩ በኋላ ሕይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል።
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ቃልአቀባይ አቶ ጅረኛ ጉዴታ፣ ታጣቂዎቻቸውን ሲቪሎችን ዒላማ እንደማያደርጉ ገልጸው አስተባብለዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡
መድረክ / ፎረም