ቤጂንግ "በዘፈቀደ የተፈጸመ" ላለችው የትራምፕ አስተዳደር ለደነገገው ተጨማሪ የቀረጥ የአጸፋ መልስ እሰጣለሁ ስትል አስጠንቅቃለች።
የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በዛሬው ዕለት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ “መልካምን በክፉ ትመልሳለች” ሲሉም ዩናይትድ ስቴትስን ወንጅለዋል።
የአሜሪካ ድምጹ ቢል ጋሎ እንደዘገበው፣ ይህ ቤጂንግ ራሷን ለዓለም መረጋጋት የቆመ ኃይል አድርጋ ለማሳየት የምታደርገው ጥረት አካል መሆኑን ጠቁሟል።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም