97ኛው የዓመታዊው የምርጥ ሲኒማ ስራዎች ሽልማት የሆነው ኦስካር በትላንትናው ምሽት በሎስ አንጀለስ ከተማ ተካሂዷል።
ኤድሪያን ብሮዲ መሪ ተዋናይ ሆኖ በተጫወተበት ‘ብሩታሊስት በተሰኘው ፊልም ላይ ላሳየው ድንቅ አጨዋወት አሸናፊ በመሆን ለሁለተኛ ጊዜ የዓመቱን ምርጥ ተዋናይነት ክብር ሲጎናጸፍ፤ ሚኪ ማዲሰን "ሞር" በተሰኘው ፊልም ላይ ላሳየችው አጨዋወት ከሴት ተዋናዮች የዓመቱ ምርጥ ለመሆን በቅታለች።
አምስት ሽልማቶች የሰበሰበው “አኖራ” የተሰኘውም ፊልም በአንጻሩ የዓመቱ ምርጥ ሆኗል።
***
ኪራን ከልኪን ሌላው የምሽቱ ባለ ድል ነው። "ኤ ሪል ፔይን" በተሰኘው ፊልም አጨዋወቱ ለዓመቱ ምርጥ ደጋፊ ተዋናይ የተቀመጠውን ሽልማት ሲረከብ፤ ዘዊ ሳልዳና በ"ኤሚሊያ ፔሬዝ" ፊልም ላይ ላሳየችው ድንቅ አጨዋወት በተመሳሳይ በሴት ተዋናዮች ጎራ በሁለተኛው እርከን የሚገኘውን ይሕን ሽልማት ወስዳለች።
ምሽቱ ድል ከቀናቸው ምርጦች ሁሉ ለፊልም ሰሪው ሻን ቤከር በእጅጉ የተዋበ ምሽት ነበር። ከፍተኛ አድናቆት ባተረፈው ‘አኖራ’ በተሰኘው የፊልም ሥራው የ97ተኛውን ኦስካር ሶስት ግዙፍ ሽልማቶች ነው ጠራርጎ የሄዴው። የዓመቱ ምርጥ ሲኒማ ድርሰት፣ ምርጥ ድሬክተር እና ምርጥ አቀናባሪ ለመባልም በቅቷል።
በምርጥ አኒሜሽን በተባለው የሲኒማ ዘርፍ ለሽልማት ከታጩት ሥራዎች “ፍሎው” የተሰኘው ፊልም “ዘ ዋይል ሮቦት” የተሰኘውን አድናቆት ያተረፈ ፊልም ሲያሸንፍ ፖል ታዜዌል ደግሞ ‘ዊክድ በተሰኘው ፊልም አልባሳት ዲዛይን ለኦስካር ሽልማት በመብቃት በዘርፉ በማሸነፍ የመጀመሪያው ጥቁር ሆኗል።
*****
የ97ተኛውን የኦስካር ተሸላሚዎች ሙሉ ዝርዝር ይህን ይመስላል:
የዓመቱ ምርጥ ሲኒማ፡ "አኖራ"
የዓመቱ ምርጥ መሪ ተዋናይ፡ አድሪያን ብሮዲ (በ’ብሩታሊስት’ ፊልም)
ሴት ምርጥ ተዋናይት፡ ሚኪ ማዲሰን (በ"አኖራ" ፊልም)
ምርጥ ድሬክተር ፡ ሻን ቤከር (በአኖራ" ፊልም)
ምርጥ ደጋፊ ተዋናይ፡ ኪራን ከልኪን (“ሪል ፔይን)
ምርጥ ሴት ደጋፊ ተዋናይ፡ ዞዊ ሳልዳና (በ"ኤሚሊያ ፔሬዝ" ፊልም)
በአለም አቀፍ የሲኒማ ሥራዎች ዘርፍ፡ ("አይ አም ስቲል ሂር")
በዘጋቢ ፊልም ዘርፍ፡ ("ኖ አዘር ላንድ")
የዓመቱ ምርጥ የሲኒማ ድርሰት፡ "አኖራ" ... ሻን ቤከር
የውርስ ትርጉም የሲኒማ ድርሰት ... "ኮንክሌቭ" ... ጸሃፊው ፒተር ስትራውገን
በወጥ የሲኒማ ሙዚቃ ...“ብሩታሊስት” ... ዳንኤል ብሉምምበርግ
በዚኒማ ዘፈን ... "ኢል ማል" ... ከ"ኤሚሊያ ፔሬዝ"
አኒሜሽን ፊልም ... "ፍሎው"
የምስል ቅንብር ... "ዱኔ ... ክፍል ሁለት"
የአልባሳት ዲዛይን ... "ዊክድ" ... ፖል ታዝዌል
ሲኒማቶግራፊ ... "ብሩታሊስት" ... ሎል ክራውሊ
በአጫጭር ዘጋቢ ፊልሞች ጎራ ... "ዘ ኦንሊ ገርል ኢን ዘ ኦርኬስትራ"
ምርጥ የድምፅ ግብአት ... "ዱኔ - ክፍል ሁለት"
የምርት ቅንብር ... "ዊክድ"
ሜካፕ እና የፀጉር አሠራር .. "ዘ ሰብስታንስ"
በፊልም አርትኦት .. "አኖራ" .. ሽን ቤከር
በአጫጭር የአክሽን ፊልም ጎራ .. “አይ አም ኖት ኤ ሮቦት"
አኒሜትድ አጭር ፊልም ዘርፍ .. "ኢን ዘ ሻዶ ኦፍ ሳይፕረስ" ... ናቸው።
መድረክ / ፎረም