ኢትዮጵያውያን የአገራቸውን ነጻነት ለማስከበር ለመጀመሪያ ጊዜ “ብሔራዊ ሆነው” የተነሡበትና በኅብረት ተዋግተው ያሸነፉበት፣ 129ኛው የዓድዋ ድል በዓል በትግራይ ክልል በሶሎዳ ተራራ ላይ ዛሬ የካቲት 23 ቀን 2017 ዓ.ም ተከበረ። በበዓሉ አከባበር ላይ የተገኙት፣ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ምኒስትር ዴኤ'ታ እንደገና አበበ፣ የዓድዋ ድል ለኢትዮጵያ እና ጭቁን ሕዝቦች ዐዲስ ምዕራፍ የከፈተ እንደነበር አስታውሰዋል።
በየዓመቱ በአገር አቀፍ ደረጃ በድምቀት የሚዘከረው የዓድዋ ድል፣ መከበር የጀመረው ጦርነቱ ከተደረገበት 1888 ዓ.ም. ከሰባት ዓመት በኋላ ነው፡፡ ዛሬ በሶሎዳ ተራራ ላይ በተከበረው በዓል ላይ፣ በጦርነቱ ጊዜ ኢትዮጵያውያን በሕብር አድርገውት የነበረውን ተሳትፎ የሚያስታውሱ የኪነጥበብ ሥራዎች ቀርበዋል።
Embed
share
Embed
share
The code has been copied to your clipboard.
The URL has been copied to your clipboard
No media source currently available
ቀጥተኛ መገናኛ
የትግራይ ክልል ባህልና ቱሪዘም ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አፅብሃ ገብረእግዚአብሄር፣ የዓድዋ ድል በዓል ለሰላም፣ አንድነት እና ብሩህ ተስፋ፣ በሚል መሪ ሐሳብ በመከበር ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም