በየዓመቱ በአገር አቀፍ ደረጃ በድምቀት የሚዘከረው የዓድዋ ድል፣ መከበር የጀመረው ጦርነቱ ከተደረገበት 1888 ዓ.ም. ከሰባት ዓመት በኋላ ነው፡፡ ዛሬ በሶሎዳ ተራራ ላይ በተከበረው በዓል ላይ፣ በጦርነቱ ጊዜ ኢትዮጵያውያን በሕብር አድርገውት የነበረውን ተሳትፎ የሚያስታውሱ የኪነጥበብ ሥራዎች ቀርበዋል።
የትግራይ ክልል ባህልና ቱሪዘም ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አፅብሃ ገብረእግዚአብሄር፣ የዓድዋ ድል በዓል ለሰላም፣ አንድነት እና ብሩህ ተስፋ፣ በሚል መሪ ሐሳብ በመከበር ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።