በተለያዩ የአውሮፓ አገሮች የጦር መሳርያዎችን በመደበቅ እና በማከማቸት የተጠረጠሩ አራት ግለሰቦች ጉዳይ ዛሬ ማክሰኞ ጀርመን ውስጥ መታየት ጀምሯል።
አራቱ ሰዎች ዩናይትድ ስቴትስ በአሸባሪነት የፈረጀችው ሐማስ አባላት ናቸው።
የጀርመኑ ዋና ዐቃቤ ሕግ ግለሰቦቹን “የውጭ አገር አሸባሪ ድርጅት አባል ናቸው” ሲሉ ከሰዋል። የጀርመኑ የዜና ወኪል ዲፓ አክሎ እንደዘገበው ጉዳዩ ለጀርመናውያኑ ዐቃብያነ-ሕግ ከሙከራ የሚታይ ነው።
“ጀርመን በውጭ አሸባሪነት በተፈረጀው ሐማስ በአባልነት በመሳተፍ የተጠረጠሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ክስ ቀርቦባቸዋል” ሲሉ ከዐቃብያነ ሕጉ አንዱ የሆኑት ጆቸን ዌይንጋርተን መናገራቸውን ዲፓ ዘግቧል።
“ሰዎቹ ከዓመታት በፊት የጦር መሳሪያ ማከማቻዎችን በማበጀት እና በመላው አውሮፓ አዳዲሶችን በመገንባት፤ ሐማስ በእስራኤል እና በአህጉሪቱ በሚገኙ የአይሁዳውያን ዒላማዎች ላይ ለሚፈጽማቸው የሽብር ጥቃቶች የታቀዱ ናቸው” ሲሉ ዐቃብያነ ሕጉ ባለፈው ዓመት ባቀረቡት ክስ መወንጀላቸው ተዘግቧል።
መድረክ / ፎረም