በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታጋቾቿ 'አሸማቃቂ' በሆነ መንገድ ተለቀዋል ያለቸው እስራኤል የፍልስጤም እስረኞችን የመልቀቁን ሂደት አዘገየች


ለ15 አመታት በእስራኤል እስርቤት ያሳለፈውን የወንድሟን አህመድ አል-ሰይፊን መፈታት ስትጠባበቅ የነበረችው ናዲን - የካቲት 23፣2025
ለ15 አመታት በእስራኤል እስርቤት ያሳለፈውን የወንድሟን አህመድ አል-ሰይፊን መፈታት ስትጠባበቅ የነበረችው ናዲን - የካቲት 23፣2025

እስራኤል ቀጣዮቹ ታጋቾቿ መፈታታቸው እስከሚረጋገጥ እና በጋዛ በሚካሄደው የእስረኛ ልውውጥ ወቅት ይፈፀማል ያለችው አሸማቃቂ ሥነስርዓት እስከሚነሳ ድረስ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ የፍልስጤም እስረኞችን የመልቀቁን ሂደት ማዘግየቷን አስታውቃለች።

የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ፅህፈት ቤት ዛሬ እሁድ ያወጣው መግለጫ ይፋ የሆነው እስረኞችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች ከኦፈር ማረሚያ ቤት እየወጡ ባሉበት ወቅት ሲሆን፣ መኪናዎቹ አዙረው ወደ እስርቤቱ ተመልሰዋል።

ስድስቱ የእስራኤል ታጋቾች ቅዳሜ እለት መለቀቃቸውን ተከትሎ ከእስር መፈታት የነበረባቸው 620 የፍልስጤም እስረኞች እስካሁን እንዳልተፈቱም ተገልጿል። ይህ ድንገተኛ የእስራኤል መግለጫ፣ የተኩስ ማቆሙን ስምምነት እጣፈንታ ጥርጣሬ ላይ ጥሎታል።

የእስረኞቹ መፈታት መዘግየቱን የፍልስጤም አስተዳደር እስረኞች ጉዳይ ኮሚሽን ያስታወቀ ሲሆን ዌስት ባንክ ውስጥ የተቀረፀው የአሶሽዬትድ ፕሬስ ምስል፣ የእስረኛ ቤተሰቦች እጅግ በጣም በሚቀዘቅዘው አየር ውስጥ ሆነው ሲጠባበቁ እና በመጨረሻ ሲበተኑ ያሳያል።

ቅዳሜ እለት የተለቀቁት ስድስቱ ታጋቾች፣ በመጀመሪያው ዙር የተኩስ ስምምነት ይለቀቃሉ ተብለው ከተጠበቁት በህይወት ያሉ የመጨረሻዎቹ ታጋቾች ሲሆኑ፣ ይህ ዙር ከአንድ ሳምንት በኃላ ይጠናቀቃል። ለሁለተኛው ዙር የተኩስ ስምምነት የሚደረገው ድርድር ገና አለመጀመሩም ተመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG