ሚያንማር እና የቅርብ አጋሯ ሩሲያ፣ ዳዌይ በተሰነው ልዩ የኢኮኖሚ ዞን፣ የወደብ እና የነዳጅ ማጣሪያ ግንባታን ያካተተ የመዋዕለ ንዋይ ትብብር መፈራረማቸውን የሩሲያ የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ዛሬ እሁድ አስታውቋል።
የሩሲያ ሚኒስትሩ ማክሲም ሪሼንትኒኮቭ እና የሚያንማር የመዋዕለ ንዋይ እና የውጭ ኢኪኖሚ ግንኙነት ሚኒስትር ካን ዛው ስምምነቱን የተፈራረሙት፣ የሩሲያ ልዑካን ቡድን ደቡብ ምስራቃዊዋን የእስያ ሀገር በጎበኙበት ወቅት ነው።
የሩሲያው ሚኒስቴር መስሪያቤት ሪሼንትኒኮቭን ጠቅሶ ባወጣው መግለጫ "ስምምነቱ በሚያንማር ከሚገኙ የሩሲያ ኩባንያዎች ጋር በጋራ የሚተገበሩ በርካታ ትላልቅ መሠረተ ልማት እና የኢነርጂ ፕሮጀክትን ያካትታል" ብሏል።
ፕሮጀክቱ ወደብ፣ በድንጋይ ከሰል የሚሰራ የሙቀት ኃይል ማመንጫ እና የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካን እንደሚያካትትም በመግለጫው ተመልክቷል።
እ.አ.አ በየካቲት 2021 በሚያንማር በተካሄደ መፈንቅለ መንግስት የኦንግ ሳን ሱ ኪ መንግስት ከስልጣን ከወረደ ወዲህ ሩሲያ የሚያንማር የቅርብ አጋር የሆነች ሲሆን ሞስኮ እና ኔይፒዳ፣ በኃይል ግንባታ ዙሪያ የሚያደርጉትን ትብብር ለማጠናከር ሲወያዩ መቆየታቸው ይታወሳል።
መድረክ / ፎረም