በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቫቲካን ሊቀ ጳጳሱ ሳይኖሩ የቅዱስ ዓመቷ ክብረ በዓልን እያከናወነች ነው 


ፎቶ ፋይል፡ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ውስጥ በ2025 የካቶሊክ ቅዱስ ዓመት ስነስርዓት ላይ፡ የካቲት 9 ቀን 2017.
ፎቶ ፋይል፡ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ውስጥ በ2025 የካቶሊክ ቅዱስ ዓመት ስነስርዓት ላይ፡ የካቲት 9 ቀን 2017.

የሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ አባ ፍራንሲስ ከገጠማቸው የሳንባ ምች እና የተወሳሰበ የመተንፈሻ አካላት በሽታ ጋር እየታገሉ ሲሆን ቫቲካን ያለ እርሳቸው የቅዱስ ዓመት ክብረ በዓልን እያከበረች ትገኛለች፡፡

አባ ፍራንሲስ ዛሬ ሌሊት በደንብ ተኝተው ማሳለፋቸውን የቫቲካን ቃል አቀባይ ማትዮ ብሩኒ ስለላሉበት የጤና ሁኔታ በተመለከተ በሰጡት አጭር መግለጫ ተናግረዋል።

ነገር ግን ዶከተሮች የ88 ዓመቱ ሊቀ ጳጳስ የገጠማቸው ህመም የተወሳሰበ የሳምባ ምች ሊያስከትል የሚችል የደም 'ኢፌክሽን' ሊሆን እንደሚችል ስጋታቸውን በመግለጥ እያሰጠነቀቁ ነው፡፡

እስከትላንት ምሽት ድረስ ግን በሽታው ይህ ስለመሆኑ ማረጋገጫ አለማግኘታቸውንና ስለሚወስዷቸው መድሃኒትቶችም ሊቀ ጳጳሱ ምላሽ እንደሚሰጡ የህክምና ቡድኑ ያሉበትን ሁኔታ በተመለከተ በሰጠው የመጀመርያ ማብራርያው ላይ አስታውቋል፡፡

የ88 ዓመቱ ሊቀ ጳጳስ ከአንድ ሳምንት በላይ በመተንፈሻ አካላት በሽታ ሲሰቃዩ ቆይተው ባለፈው ሳምንት ሮም በሚገኘው ገሚሊ ሆስፒታል ገብተዋል።

ከአውሮፓዊያኑ 2013 ዓ.ም ጀምሮ በሊቀ ጳጳስነት መንበራቸው የቀጠሉት ፍራንሲስ፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በተደጋጋሚ የኢንፍሉዌንዛ እና ሌሎች የጤና ችግሮች አጋጥሟቸዋል።

በልጅነታቸው ፕለረሲ በተባለ በሽታ በመጠቃታቸው ከአንደኛው የሳንባ ክፍል የተወሰነው በቀዶ ጥገና እንዲወገድ ተደርጓል። በቅርብ ጊዜያት ውስጥ ሊቀ ጳጳሱ ለሳንባ መቆጣት ተጋላጭ ኾነዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG