በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ የላከቻቸው አብዛኞቹ  ፍልሰተኞች ወደየሀገራቸው ለመመለስ መስማማታቸውን ፓናማ ተናገረች


በቅርብ ቀናት ከዩናይትድ ስቴትስ ፓናማ ወደሚገኙ ማሸጋገሪያ ጣቢያዎች ከተላኩት ፍልሰተኞች ውስጥ ከግማሽ በላዩ በፈቃደኝነት ወደየሀገራቸው ለመመለስ መስማማታቸውን የፓናማ የደኅንነት ሚንስትር ተናገሩ፡፡
በቅርብ ቀናት ከዩናይትድ ስቴትስ ፓናማ ወደሚገኙ ማሸጋገሪያ ጣቢያዎች ከተላኩት ፍልሰተኞች ውስጥ ከግማሽ በላዩ በፈቃደኝነት ወደየሀገራቸው ለመመለስ መስማማታቸውን የፓናማ የደኅንነት ሚንስትር ተናገሩ፡፡

በቅርብ ቀናት ከዩናይትድ ስቴትስ ፓናማ ወደሚገኙ ማሸጋገሪያ ጣቢያዎች ከተላኩት ፍልሰተኞች ውስጥ ከግማሽ በላዩ በፈቃደኝነት ወደየሀገራቸው ለመመለስ መስማማታቸውን የፓናማ የደኅንነት ሚንስትር ተናገሩ፡፡ የሚበዙት የእስያ ወይም የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገር ተወላጆች መኾናቸው ተመልክቷል፡፡

የፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ አስተዳደር በሕገ ወጥ ፍልሰት ላይ እየወሰደ ባለው ርምጃ በቅርቡ ፍልሰተኞቹን በሦስት አውሮፕላኖች አሳፍሮ ወደ ፓናማ ልኳቸዋል፡፡ ቁጥራቸው ወደ 299 የሚጠጋው ፍልሰተኞች ፓናማ ሲቲ በሚገኝ ሆቴል በሀገሪቱ ባለሥልጣናት ጥበቃ ሥር ሆነው እንዲቆዩ የተደረገ ሲሆን ዩናይትድ ስቴትስ በዓለም አቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት (አይ ኦ ኤም) እና በመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን (ዩ ኤን ኤች ሲ አር) በኩል የገንዘብ ድጋፍ እያደረገች መሆኑን የፓናማው ሚንስትር ፍራንክ አብሬጎ ከትላንት በስቲያ ማክሰኞ በሰጡት መግለጫ አመልክተዋል፡፡

"171 ፍልሰተኞች ለመመለስ ፈቃደኛ ሆነዋል፡፡ የተቀሩትም ተመድ መጓጓዣቸውን እንዳዘጋጀላቸው ቀስ በቀስ ይመለሳሉ" ብለዋል ሚንስትሩ፡፡ እስከዚያው በደቡባዊ ፓናማ ዳሪየን ጋፕ በሚባለው ደን አቅራቢያ ወደሚገኝ መጠለያ ጣቢያ ሳይዛወሩ እንደማይቀር ተጠቁሟል፡፡

ባለፈው ወር ከዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋራ የተነጋገሩት የፓናማ ፕሬዝደንት ሆዜ ራኡል ሙሊኖ በሐምሌ ወር ከዩናይትድ ስቴትስ የሀገር ደኅንነት ሚንስቴር ጋራ የተደረሰውን ስምምነት በማስፋት የቬንዙዌላ፣ ኢኳዶር እና ኮሎምቢያ ፍልሰተኞችንም ወደፓናማ ለመመለስ እንዲያስችል ለማድረግ እንደሚቻል ማስታወቃቸው ይታወሳል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG