በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩክሬን ችግር ከመፈታቱ በፊት አሜሪካና ሩሲያ መተማመን እንደሚያስፈልጋቸው ፑቲን አስታወቁ


 የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሴንት ፒተርስፕርግ በተካሄደ ክብረ በዓል ላይ ንግግር ሲያደርጉ፣ የካቲት 12 ቀን 2017 ዓ.ም.
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሴንት ፒተርስፕርግ በተካሄደ ክብረ በዓል ላይ ንግግር ሲያደርጉ፣ የካቲት 12 ቀን 2017 ዓ.ም.

ከዩክሬን ጋራ ያለው ጦርነት መፍትሔ ከማግኘቱ በፊት፣ ሃገራቸው ከአሜሪካ ጋራ ያላትን የመተማመን ሁኔታ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ዛሬ አስታውቀዋል።

በሳዑዲ አረቢያ አስተናጋጅነት በሩሲያ እና በአሜሪካ ባለሥልጣናት መካከል የተደረገው ንግግር ውጤት እንዳስደሰታቸው የገለጹት ፑቲን፣ ንግግሩ በዋሽንግተን እና በሞስኮ መካከል የሚታየውን አጨቃጨቂ ግንኙነት ለማሻሻል የመጀመሪያው ርምጃ እንደሆነ አመልክተዋል።

ነገር ግን “በአሜሪካና በሩሲያ መካከል መተማመን ከሌለ፣ የዩክሬኑንም ሆነ ሌሎችን ችግሮች ለመቅረፍ አይቻልም” ሲሉ አክለዋል።

ፑቲን ከአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ጋራ መነጋገር እንደሚሹ አስታውቀው፣ ”ውጤት እንዲያመጣ ግን ዝግጅት መደረግ አለበት” ብለዋል።

የዩክሬንም ሆነ የአውሮፓ ባለሥልጣናት በሳዑዲው ንግግር ላይ አልትገኙም። ነገር ግን ወደፊት በሚደረጉ ድርድሮች ላይ እንደሚሳተፉ አሜሪካ አስታውቃለች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG