በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሳዑዲው አልጋ ወራሽ የዩክሬንና የጋዛን ጦርነት ለማስቆም ወሳኝ ሚና እየተጫወቱ ነው ተባለ


የሳውዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ መሀመድ ቢን ሳልማን ከዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር በሪያድ ፣ ሳዑዲ አረቢያ በተወያዩበት ወቅት ፣ የካቲት 10 ቀን 2017 ዓ.ም.
የሳውዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ መሀመድ ቢን ሳልማን ከዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር በሪያድ ፣ ሳዑዲ አረቢያ በተወያዩበት ወቅት ፣ የካቲት 10 ቀን 2017 ዓ.ም.

የሳዑዲው አልጋ ወራሽ፣ ትረምፕ የዩክሬንና የጋዛን ጦርነት ለማስቆም ለሚያደርጉት ጥረት ወሳኝ ሚና እንዳላቸው አሳይተዋል ተባለ።

በአሜሪካና በሩሲያ ባለሥልጣናት መካከል በዩክሬን ጉዳይ ላይ የተደረገውን ስብሰባ ያስተናገዱት አልጋ ወራሽ ሞሃመድ ቢን ሳልማን፣ በመቀጠል ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ አሜሪካ ጋዛን እንድታስተዳድር ያቀረቡትን ሃሳብ በተመለከተ ከግብፅ፣ ዮርዳኖስ፣ ቃጣር እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መሪዎች ጋራ የአረቡን ዓለም ምላሽ በተመለከተ ለመወያየት ጉባኤ ያስተናግዳሉ።

“ሁለቱ ጉባኤዎች ትረምፕ የዩክሬንና የጋዛን ጦርነት ለማስቆም በምርጫ ዘመቻቸው ወቅት የገቡትን ቃል ተግባራዊ ለማድረግ የአልጋ ወራሹ እያደገ የመጣ ሚና መኖሩን የሚያመለከት ነው” ስትል የቪኦኤ የዋይት ሃውስ ሃላፊ ፓትሲ ዊዳኩስዋራ በዘገባዋ አመልክታለች።

የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ ሃገራቸው በሪያዱ ጉባኤ አለመጋበዟ እንዳሳሰባቸው እየገለጹ ቢሆንም፣ የአሜሪካው ፕሬዝደንት በፍሎሪዳ ከሚገኘው ማር አ ላጎ መኖሪያቸው ባስተላለፉት መልዕክት “ይህን ጦርነት ለማስቆም ጉልበቱ አለኝ” ብለዋል።

የሳዑዲው ጉባኤ በአሜሪካና በሩሲያ መካከል ውጥረት ይታይበት የነበረው ግንኙነት መርገቡን የሚያሳይ ሲሆን፣ ሩሲያን አግልሎ ዩክሬንን መደገፍ ላይ ያተኮረው የቀድሞው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ፖሊሲ ማክተሙንም የሚያመለከት ነው ተብሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG