በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

 
አባ ፍራንሲስ  ጠንከር ያለ ሕመም ስለገጠማችው ቫቲካን የሳምንት መገባደጃ መርሐ ግብራቸውን ሰረዘች 

አባ ፍራንሲስ  ጠንከር ያለ ሕመም ስለገጠማችው ቫቲካን የሳምንት መገባደጃ መርሐ ግብራቸውን ሰረዘች 


ፋይል፡ የሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ አባ ፍራንሲስ በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ፣ የካቲት 2 2017 ዓ.ም.
ፋይል፡ የሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ አባ ፍራንሲስ በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ፣ የካቲት 2 2017 ዓ.ም.

ሐኪሞች ህመማቸው ጠንከር ያለ እንደሆነ በመግለጻቸው ምክንያት ላለፉት አምስት ቀናት ሆስፒታል ውስጥ የቆዩት የሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ አባ ፍራንሲስ ለሳምንቱ መገባደጃ በተያዙት መርሐ ግብሮች ላይ እንደማይገኙ ቫቲካን በዛሬው ዕለት አስታወቀች ።

የ88 ዓመቱ ሊቀ ጳጳስ ከአንድ ሳምንት በላይ በመተንፈሻ አካላት በሽታ ሲሰቃዩ ቆይተው አርብ ዕለት ሮም በሚገኘው ገሚሊ ሆስፒታል ገብተዋል።

ቅዳሜ ሊካሄድ የታቀደው የቡራኬ ሥነ ስርዐት “በቅዱስ አባታችን የጤና ሁኔታ ምክንያት ተሰርዟል” ስትል ቫቲካን ባሰራጨችው አጭር መግለጫ ተመላክቷል።

ዘወትር እሑድ ረፋድ ላይ ለቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ምዕመንና ታዳሚ በመስኮት ሰላምታ የሚሰጡበትና የሚባርኩበት ሥርዐት በምክትል የቫቲካን ሹም በኩል እሑድ ዕለት እንደሚከናወን ተገልጿል።

ቫቲካን ሰኞ ዕለት እንዳስታወቀችው ሐኪሞች የጳጳሱን መድኃኒት ለሁለተኛ ጊዜ ቀይረዋል። ሐኪሞች ሊቀ ጳጳሱ የገጠማቸውን የጤና ችግር "ፖሊሚክሮቢያል ኢንፌክሽን" ብለው ገልጸውታል።

ሐኪሞቹ በሽታው በቫይረስ ፣ ባክቴሪያ እና ፈንገስ ድብልቅ ተውሳኮች ሊቀሰቀስ እንደሚችል ተናግረዋል።

ከአውሮፓዊያኑ 2013 ዓ.ም ጀምሮ በሊቀ ጳጳስነት መንበራቸው የቀጠሉት ፍራንሲስ፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በተደጋጋሚ የኢንፍሉዌንዛ እና ሌሎች የጤና ችግሮች አጋጥሟቸዋል።

በልጅነታቸው ፕለረሲ በተባለ በሽታ በመጠቃታቸው ከአንደኛው የሳንባ ክፍል የተወሰነው በቀዶ ጥገና እንዲወገድ ተደርጓል። በቅርብ ጊዜያት ውስጥ ሊቀ ጳጳሱ ለሳንባ መቆጣት ተጋላጭ ኾነዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG