አፍሪካ ኅብረት እና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለፕሪቶሪያው ስምምነት ተፈጻሚነት ትኩረት እንዲሰጡ የትግራይ ክልል ጥሪ አቀረበ።
የፕሪቶሪያውን ስምምነት አጠቃላይ ሂደት እና ከሂደቱ ተገኙ የተባሉ ትምህርቶችን በተመለከተ በአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ ይፋ ተደርጓል።
ሪፖርቱ ይፋ በኾነበት ወቅት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ባቀረቡት ጥሪ፣ እስካሁን አልተፈጸሙም ያሏቸው የስምምነቱ ነጥቦች እንዲፈፀሙ የአፍሪካ ኅብረትና እና ዓለምዓቀፉን ማኅበረሰብ ትኩረት ጠይቀዋል።
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ በበኩላቸው፣ ቀጣይ ሂደቶች በውይይትና ሕግን ባከበረ መልኩ መተግበር አለባቸው ብለዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም