በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩስያ ወታደሮች በምስራቅ በዩክሬን ሃይሎች ላይ ጥቃቱን አጠናክረው ቀጥለዋል  


 ፋይል፡ የዩክሬን ወታደሮች በፖክሮቭስክ ከተማ አቅራቢያ ወደ ሩሲያ ወታደሮች ሲተኩሱ ያሳያል፡፡
ፋይል፡ የዩክሬን ወታደሮች በፖክሮቭስክ ከተማ አቅራቢያ ወደ ሩሲያ ወታደሮች ሲተኩሱ ያሳያል፡፡

የሩስያ ወታደሮች በምስራቃዊ ዩክሬን ጥቃታቸውን በከፍተኛ ሁኔታ አጠናክረዋል ሲል የኪዬቭ ጦር አስታውቋል፡፡

አንድ የኔቶ ባለስልጣን ሞስኮ ጦርነቱን ለመጨረስ በሚደረገው ውይይት የጥቃቱን ፍጥነት እና ጥንካሬ እንደሚጨምር ተንብየዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሰላም እንዲሰፍን ግፊት እያደረጉ ባሉበትና የአሜሪካና ሩሲያ ባለስልጣናት በሚቀጥሉት ቀናት በሳውዲ አረቢያ ይገናኛሉ ትብሎ በሚጠበቅበት በአሁኑ ወቅት የሩስያ ጦር የተከፈተው ዋናዎቹ ጥቃቶቹ ያተኮሩት በፖክሮቭስክ የሎጂስቲክስ ማእከል አቅራቢያ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የኪየቭ ጦር ትላንት ከሩሲያ ጋር በ24 ሰዓት ጊዜ ውስጥ 261 ውጊያዎች ማድረጉን ገልጿል፣ ይህም በዚህ አመት ከፍተኛው ቁጥር ሲሆን በቀደሙት ቀናት ከተመዘገበው በመቶ እጥፍ የሚበልጥም ነውም ብሏል፡፡

የዩክሬን ወታደራዊ መረጃ እንደሚያመለክተው የሞስኮ ወታደሮች በእኤአ 2024 አጋማሽ ጀምሮ በምስራቅ በኩል መንደር በመንደር ቀስ በቀስ የገፉ መምጣታቸውን አስታውቀዋል። ምንም እንኳን ፕሬዚደንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በምስራቅ በኩል “ ጥሩ ውጤት” ተገኝቷል ያሉ ቢሆንም፡፡

የወታደራዊ ሃይሉ ቃል አቀባይ በበኩላቸው የኪየቭ ሀይሎች የፒሽቻን መንደር መልሰው መያዛቸውን ተናግረዋል።

ፕሬዘዳንት ትራምፕ በመጀመሪያ ኪዬቭ ጋር ሳይማክሩ እና አውሮፓውያንን ሙሉ በሙሉ ለመተው ከሩሲያውያን ጋር በቀጥታ ለመገናኘት መገፋፋቸው በዩክሬን እና በአውሮፓ በኩል አስደንጋጭ ሁኗል ። የዩክሬን ባለስልጣናትም ትራምፕን ለማወደስ ጥንቃቄ አድርገዋል፡፡

ኪየቭ በሳዑዲ አረቢያ በሚደረገው ድርድር ላይ ለመሳተፍ እንዳልተጋበዘችና በማንኛውም ሁኔታ ከሩሲያ ባለስልጣናት ጋር ከመገናኘቷ በፊት ከአሜሪካ እና ከአውሮፓ አጋሮቿ ጋር የጋራ ስትራቴጂ መንደፍ እንደምትፈልግ አስታውቃለች።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG