በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደቡብ አፍሪካውያን ነጮች ትራምፕን በመደገፍ ሰልፍ አካሄዱ 


ደቡብ አፍሪካውያን ነጮች ፕሪቶሪያ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት ሰልፍ ወጥተው ይታያል፡፡ የካቲት 8 2017 ዓም፡፡
ደቡብ አፍሪካውያን ነጮች ፕሪቶሪያ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት ሰልፍ ወጥተው ይታያል፡፡ የካቲት 8 2017 ዓም፡፡

አንዳንድ ደቡብ አፍሪካውያን ነጮች ትላንት ቅዳሜ ፕሪቶሪያ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ተሰባስበው ለፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያላቸውን ድጋፋ የገለጡ ሲሆን በገዛ መንግሥታቸው የዘረኝነት ሰለባ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

በመቶዎች የሚቆጠሩት ሰልፈኞቹ “ለፕሬዚዳንት ትራምፕ ፈጣሪ ይመስገን” የሚል ፅሁፎችን የያዙ እና በደቡብ አፍሪካ መንግስት የታወጀና አናሳ ነጭዎችን ለአድሎ የሚዳርግ የዘረኝነት ህግ ነው ያሉትንም የሚተቹ ሌሎች መፈክሮችን ይዘው ታይተዋል።

የደቡብ አፍሪካ መንግስት በበኩሉ አዲሱ ህግ ከዘር ጋር የተያያዘ ነው ሲሉ ፕሬዘዳንት ትራምፕ በሀገሪቱ እና በህጉ ላይ ያነሱት ጥያቄ የተሳሳተ መረጃ እና የተዛባ ነው ሲል አስተባብሏል፡፡

የትራምፕ አስተዳደር በደቡብ አፍሪካ ላይ የሰነዘረው ትችት እና ቅጣት በሀገሪቱ ለዘመናት የዘለቀው የአናሳ ነጮች አገዛዝና በጥቁሮች ላይ ያደረሱትን የጭቆና ጥፋቶችን ለመፍታት እየተወሰደ ያለውን ርምጃ አሳሳቢነት ከፍ አድርጎታል፡፡

የደቡብ አፍሪካ መንግሥት እንደሚለው፣ የመሬት ሕጉ አብዛኛው የእርሻ መሬቶች የአገሪቱ ሕዝብ 7 በመቶው ብቻ በሆኑ ነጮች ባለቤትነት የተያዘውን በእኩልነትና ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ለማከፋፈል ያለመ ነው፡፡

ነጭ ሰልፈኞች ወረራ ነው ያሉትን ህግ ጨምሮ በ1994 ከአፓርታይድ ስርዐት ማብቂያ ጀምሮ ለጥቁሮች የቅድሚያ እድሎችን ለመስጠት የተደረጉ ማሻሽያዎችን የሚያመለክቱ ባነሮችን ይዘውም ታይተዋል። “ብላክ ኢኮኖሚክ ኢምፓወርመንት” በመባል የሚታወቁት እነዚህ ህጎች ለአንዳንድ ነጮች የብስጭት ምክንያት ሆነዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG