በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የታይላንድ ሠራዊት ከሚያንማር በሕገወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የተገኙ 260 ሰዎችን መረከቡን አስታወቀ


ታይላንድ 260 የሕገወጥ አዘዋዋሪ ሰለባዎች ከማይንማር ተቀብላለች፡፡
ታይላንድ 260 የሕገወጥ አዘዋዋሪ ሰለባዎች ከማይንማር ተቀብላለች፡፡

ታይላንድ 260 የሕገወጥ አዘዋዋሪ ሰለባዎች ከማይንማር ተቀብላለች፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ተገልጿል፡፡ የታይላንድ ጦር ዛሬ ሐሙስ በሰጠው ቃል ቁጥጥር በሌለው በሁለቱ ሀገሮች ድንበር አቅራቢያ የሳይበር ወንጀል ማዕከሎች ላይ ዘመቻ የከፈተችው ሚያንማር በስፋት ሰለባዎችን ወደመጡበት እየመለሰ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በታይላንድ የወንጀለኞች ቡድኖች በሁለቱ ሀገሮች ድንበር በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በሕገወጥ መንገድ በማዘዋወር፤ በደቡብ ምሥራቅ እስያ በተለይም በኢንተርኔት ሕገ ወጥ ሥራ ላይ በግዴታ በማሰማራት በየዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ገቢ እንደሚያደርጉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ገልጿል።

የታይላንድ ጦር ባወጣው መግለጫ “ቡድኑን የዜጎችን ማንነት ካጣራ በኋላ ከ20 ሀገራት የመጡ ሰዎች መኖራቸውን ለማወቅ እንደቻለ ገልጾ ከነዚህ ውስጥ 138ቱ ኢትዮጵያውያን ናቸው ብሏል።

ምንም እንኳን ህገወጥ ተግባራቱ ለብዙ ለዓመታት የነበሩ ቢሆንም፣ ቻይናዊው ተዋናይ ዋንግ ዢንግ የትወና ሥራ ታገኛለህ ተብሎ በማባበል ከታገተ ወዲህ የታይላንድ ባለሥልጣናት በሕገ ወጡ እንቅስቃሴ ላይ ላይ ዘመቻቸውን አጠናክረዋል። ተዋናዩን በኋላ የታይላንድ ፖሊስ ማይንማር አግኝቶ አስለቅቆታል፡፡

ትላንት ረቡዕ በታይላንድ ድንበር አካባቢ የሚንቀሳቀሰው የሚያንማር ሽምቅ ተዋጊ ቡድን የዴሞክራቲክ ካረን ቡዲስት ጦር፣ ሠራተኞቻቸው በቁጥጥር ስር ባሉ አካባቢዎች የግዳጅ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሰዎችን በመፈለግ ላይ ሳሉ፤ 260 የሚሆኑ ሰዎችን ምንነቱ ባልታወቀ "ሥራ" ውስጥ ተሰማርተው ማግኘቱን ተናግሯል። የቡድኑ አዛዥ ሻለቃ ሳው ሳን አውንግ ለሮይተርስ በሰጡት ቃል “እንዴት እንደመጡ አናውቅም።” ያሉ ሲሆን “በግዳጅ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሰዎችን መፈለጋችንን እንቀጥላለን እናም እንመልሳቸዋለን” በማለት ተናግረዋል፡፡

ታይላንድ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ሕገ-ወጥ ሥራዎች በሚከናወኑባቸው የምያንማር አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ፣ ነዳጅ እና የበይነ መረብ አገልግሎትን አቋርጣለች፡፡ ሁኔታው ባንኮክ የማጭበርበር ወንጀል ምን ያህል የቱሪዝም ዘርፏን እንዳናጋ እንደሚያሳይ ተገልጿል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG