በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ህወሓት ከተፈናቃዮች "በግዳጅ የገንዘብ መዋጮ በመሰብሰብ" አቤቱታ ቀረበበት


ፎቶ፦ ሽረ እንዳሥላሴ
ፎቶ፦ ሽረ እንዳሥላሴ

ህወሓት ከተፈናቃዮች "በግዳጅ የገንዘብ መዋጮ በመሰብሰብ" አቤቱታ ቀረበበት
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:36 0:00

- "ከተፈናቃዮች በፈቃዳቸው የሚያዋጡ እንጂ በዕቅድ የሚሰበሰብ የፓርቲ ገንዘብ የለም፤" /ህወሓት/

በትግራይ ክልል ሽረ እንዳሥላሴ ከተማ የሚገኙ ተፈናቃዮች፣ “ህወሓትን ለማዳን” በሚል ከእያንዳንዱ ቤተሰብ 200 ብር እንዲያዋጡ እየተገደዱ መኾናቸውን፣ ለአሜሪካ ድምፅ የተናገሩ አስተያየት ሰጪዎች ገለጹ።

በተመሳሳይ፣ የዓለም ምግብ ፕሮግራም(WFP) ለክልሉ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በጻፈው ደብዳቤ፣ "ለጥቃት ተጋላጭ የኾኑ ተፈናቃዮች፣ ለአንድ ፓርቲ በግዳጅ ብር እንዲያዋጡ ማድረግ አግባብነት የለውም፤" ሲል ወቅሷል።

በጉዳዩ ላይ ምላሽ የጠየቅናቸው፣ የትግራይ ክልል ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን የህወሓት አስተባባሪ አቶ ወልደ‍ ኣብርሃ ገብረ ፃድቕ፣ ህወሓት በየዓመቱ ለፓርቲው ማጠናከርያ ከአባሎቹ እና ደጋፊዎቹ ገንዘብ እንደሚሰበስብ አውስተው፣ "ከተፈናቃዮች ግን ገንዘብ ለመሰብሰብ አላቀደም፤" ብለዋል። ኾኖም፣ ከተፈናቃዮች መካከል በፈቃዳቸው ለፓርቲው ገንዘብ የሚሰጡ ግን መኖራቸውን ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG