ትላንት ከሰዓት በኋላ ጀምሮ ከተነሲ እስከ ፔንስልቬንያ፣ ከኒው ጀርሲ እስከ ዌስት ቨርጂንያ ሲጥል የነበረው በረዶና እጅግ የቀዘቀዘ ዝናብ ዛሬም እንደሚቀጥል ይጠበቃል።
በአንዳንድ ሥፍራዎች በአማካይ እስከ 15 ሴንቲ ሜትር በረዶ የጣለ ሲሆን፣ በዲሲና አካባቢው ግዛቶች የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞች እስከ 2 ሰዓት ያህል ዘግይተው ሥራ እንዲገቡ ተፈቅዷል። በርካታ ት/ቤቶች ሲዘጉ፣ የመኪና አደጋዎችም ተከስተዋል። በአንዳንድ ሥፍራዎችም የመብራት መቋረጥ ተከስቷል።
በሰደድ እሳት ስትለበለብ በነበረችው የካልፎርንያ ግዛት ነፋስ የቀላቀለ ዝናብ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ጎርፍ ሊከሰት እንደሚችልም ተተንብይዋል። በማዕክከላዊና ደቡብ ካልፎርኒያ የሚገኙ ከተሞችን በጎርፍ ሊያጥለቀቅ ይችላል።
የትራንስፖርት ባለሥልጣናት ስዎች ወደ አውራ ጎዳና ከመውጣት እንዲቆጠቡ መክረዋል።
በሺሕዎች የሚቆጠሩ የመብራት አገልግሎት ሠራተኞችና እንዲሁም በርካታ ቨርጂንያ የብሔራዊ ዘብና መከላከያ አባላት ከበረዶው ጋራ ተያይዞ ለሚከሰቱ ችግሮች ምላሽ ለመስጠት ተሰማርተዋል።
መድረክ / ፎረም