በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትራምፕ በዓለሙ የወንጀለኞች ችሎት ላይ ማዕቀብ ጣሉ


የአለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት - አይሲሲ
የአለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት - አይሲሲ

ፕሬዝደንት ትረምፕ በመጀመሪያው የሥልጣን ዘመናቸው የወሰዱትን እርምጃ በመድገም፤ በአሜሪካ ዜጎች ላይ ወይም እንደ እስራኤል ባሉ አጋሮቻቸው ላይ ምርመራ ባደረጉ፣ በአለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት - አይሲሲ የሚያገለግሉ ግለሰቦች ላይ የተነጣጠረ የኢኮኖሚ እና የጉዞ ማዕቀብ እንዲጣል ትዕዛዝ ሰጥተዋል።

እርምጃው በጋዛው ጦርነት ሳቢያ ከቀድሞ መከላከያ ሚንስትራቸው እና ከፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሃማስ መሪ ጋር በዓለም አቀፉ ችሎት ከሚፈለጉት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የዋሽንግተን ጉብኝት ጋር ተገጣጥሟል።

በመጀመሪያው የትራምፕ አስተዳደር እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2020 አፍጋኒስታን በሚገኙ የአሜሪካ ወታደሮች ተፈጽመዋል የተባሉ የጦር ወንጀሎች ምርመራ ሳቢያ ዋሽንግተን በአቃቤ ሕግ ፋቱ ቤንሱዳ እና በረዳታቸው ላይ ማዕቀብ መጣሏ ይታወሳል።

አይሲሲ ጉዳዩን አስመልክቶ ለቀረበለት ጥያቄ ለጊዜው ምላሽ አልሰጠም። እርምጃው ማዕቀቡ ተጣለባቸው ግለሰቦች በአሜሪካ ውስጥ ያላቸውን ማንኛውንም ዓይነት ንብረት እንዳያንቀሳቅሱ ማድረግን እና ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ ዩናይትድ ስቴትስ እንዳይጎበኙ መከልከልን ያካትታል። ዩናይትድ ስቴትስ ማዕቀብ የጣለችባቸውን ሰዎች ስም መቼ ይፋ እንደምታደርግ ለጊዜው ግልጽ አይደለም።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG