በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የባሕር ዳሩ የጥበበ ጊዮን ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ህክምና ዳይሬክተር ዶ/ር አንዱአለም ዳኜ ተገደሉ


የጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ህክምና ክፍል ዳይሬክተር የነበሩት ዶ/ር አንዱአለም ዳኜ
የጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ህክምና ክፍል ዳይሬክተር የነበሩት ዶ/ር አንዱአለም ዳኜ

በአማራ ክልል ርዕሰ መዲና ባህር ዳር የጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ህክምና ክፍል ዳይሬክተር የነበሩት ዶ/ር አንዱአለም ዳኜ ከትላንት በስቲያ ጥር 24/2017 ዓ.ም ከስራ አምሽተው ወደ ቤታቸው በመጏዝ ላይ ሳሉ በተተኮሰባቸው ጥይት መገደላቸው ተገለጠ፡፡ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ዶክተሩ የተገደሉት በዘራፊዎች ሳይሆን አይቀርም ብሏል፡፡

የባሕር ዳሩ የጥበበ ጊዮን ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ህክምና ዳይሬክተር ዶ/ር አንዱአለም ዳኜ ተገደሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:53 0:00

የመምሪያው ኃላፊ ኮማንደር ዋለልኝ ቢምረው ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት ቃል ዶክተሩ በባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሥር ባለው ጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝ ሆስፒታል ቅጽር ግቢ ውስጥ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በመሄድ ላይ ሳሉ በከተማዋ ሰባታሚት "ቆሸ" በተባለ ሥፍራ በታጣቂዎች በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸውን አጥተዋል ብለዋል::

በአካባቢው ለዝርፊያ ታጥቆ የሚንቀሳቀስ ቡድን እንዳለ ያመለከቱት ኮማንደሩ ገዳዮችን ለመያዝ ብዛት ያለው የፀጥታ ኅይል ተሰማርቷል ብለዋል::

የአማራ ክልል የጤና ባለሙያዎች ማህበር በበኩሉ በህክምና ባለሙያዎች ላይ እየደረሰ ያለው ግድያ እና እስር እያሳሰበው እንደሆነ ተናግሯል ::

ይህ በእንዲህ አንዳለ የኢትዮጵያ የጤና ሚንስቴር በፌስቡክ ገጹ ባሰፈረው ጽሁፍ በዶክትር አንዱ ዓለም ዳኘ ሕልፈተ ህይወት ሐዘኑን ገልጾ ሕብረተሰቡን በቅንነት እና በታታሪነት የሚያገለግሉ የጤና ባለሙያዎች ላይ የሚደረግ ግድያ ተቀባይነት የሌለው እና የሚወገዝ ተግባር ነው" ብሏል::

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG