በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትግራይ ክልል የፖለቲካ ኅይሎችን  ያወዛገበው አማካሪ ምክር ቤት ተቋቋመ


የክልሉ ጊዝያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ
የክልሉ ጊዝያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ
በትግራይ ክልል የፖለቲካ ኅይሎችን  ያወዛገበው አማካሪ ምክር ቤት ተቋቋመ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:50 0:00

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አማካሪ ምክር ቤት፣ ትላንት እሁድ በይፋ ተቋቁሞ ሥራ ጀመረ።

"ምክር ቤቱ የተለያዩ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸው ሰዎች የተሳተፉበት፣ እና የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ሥራዎች የሚከታተል ነው"፣ ሲሉ የክልሉ ጊዝያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ተናግረዋል።

ምክር ቤቱ አቶ ሞገስ ታፈረ ዋና ሰብሳቢ፡ የውድብ ናፅነት ትግራይ ሊቀመንበር ዶክተር ደጀን መዝገበን ደግሞ ምክትል ሰብሳቢ አድርጎ መርጧል።

በዚሁ ምክር ቤት የተጋበዙት ሳልሳይ ወያነ ትግራይ፣ የዲያስፖራ አባላት እና የጸጥታ አካላት አልተሳተፉም።

በዶክተር ደብረ ፅዮን ገብረ ሚካኤል የሚመራው የህወሐት ቡድን አማካሪ ምክር ቤቱ ህወሓት ላይ “የፖለቲካ እጥበት” ለማካሄድ የተሸረበ ሴራ ነው በማለት ተቃውሞ ማሰማቱ ይታወቃል ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG