በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትራምፕ እና ኔታኒያሁ በጋዛ፣ በኢራን እና በአረብ ሀገራት ጉዳዮች ላይ ሊወያዩ ነው


የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የፊታችን ማክሰኞ ከዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር፤ በዋይት ሀውስ ሲገናኙ፤ የኢራን ጥቃትን በመቃወም፣ ከአረብ ሀገራት ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን በማስፋፋት እንዲሁም ሀገራቸው "በሀማስ ላይ ድል" ስለማድረጓ እንደሚወያዩ በዛሬው ዕለት ተናግረዋል ።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሁለት ሳምንት በፊት ለሁለተኛ ጊዜ ለቀጣዩ አራት ዓመታት ሀገሪቱን ለመምራት ሥልጣን ከተረከቡ በኋላ የሚያገኟቸው የመጀመሪያው የውጭ ሀገር መሪ ቀዳሚው ኔታንያሁ ሊሆኑ ነው። ትራምፕ እና ኔታንያሁ የረዥም ጊዜ አጋሮች ሲሆኑ፤ ፕሬዝዳንቱ የመካከለኛው ምሥራቅ መልዕክተኛውን ስቲቭ ዊትኮፍን ልከው እስራኤል ከሃማስ ጋር በከፈተችው ጦርነት እና በእስረኞች መካከል ያለውን ልውውጥ፤ የስድስት ሳምንት የተኩስ አቁም በማድረግ እንዲያደራድሩም በማድረግ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል።

ምንም እንኳን የሃማስ ታጣቂዎች በእስራኤል ተይዘው የነበሩትን በመቶዎች የሚቆጠሩ የፍልስጤም እስረኞች ለውጥ 18 ታጋቾችን ነጻ ቢለቁም፣ ሁለተኛው የእርቁ ሂደት ከፍተኛ ተግዳሮት ገጥሞታል።

እስራኤል ይህ እንዲሆን አልፈቅድም ብላ ብትናገርም፤ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ከተደረገበት ከባለፈው ወር አንስቶ በዩናይትድ ስቴትስ አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው የሃማስ ቡድን ሙሉ ለሙሉ በድጋሚ ጋዛን በቁጥጥሩ ስር ማድረጉን አረጋጧል።

ይህን ተከትሎ፤ ጦርነቱ ሙሉ ለሙሉ ሳይቆም እና የእስራኤል ጦር በሜዲትራኒያን ባህር ዳርቻ ካለው ጠባብ የጋዛ ሰርጥ ክፍል በሙሉ ለቆ ሳይወጣ በሁለተኛው የእርቅ ሂደት ነፃ ሊወጡ የታቀዱ ተጨማሪ ታጋቾችን እንደማይለቅ ሃማስ አስታውቋል።

የመጀመሪያው የእርቅ ሂደት የፊታችን መጋቢት መጀመሪያ ላይ ካበቃ በኋላ ጦርነቱን እንዲቀጥሉ ኔታንያሁ ከቀኝ ቀኝ ዘመም አጋሮቻቸው ጫናው አይሎባቸዋል።

ይሁን እንጂ በጉዳዩ ላይ ትራምፕ ያላቸው አቋም እስካሁን ግልፅ አይደለም።

ምንም እንኳን ትራምፕ የእስራኤል ጠንካራ ደጋፊ ቢሆኑም፤ በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት በመካከለኛው ምሥራቅ ያሉትን ጦርነቶች ለማስቆም እና የተኩስ አቁም ስምምነቱን ለማደራደር ቃል መግባታቸው የሚታወስ ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG