ሩሲያ በዩክሬን ምስራቃዊ ዋና የሆንችው ቶሬትስክ ከተማ አጠገብ ያለች መንደር መያዟን ዛሬ አስታውቃለች፡፡ ኪየቭ በበኩሏ በሩሲያ ሌሊት ላይ ባደረሰችው ጥቃት አራት ሰዎች መሞታቸውን ገልጻለች።
የሩስያ መከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ወታደሮቹ በምስራቅ ዶኔትስክ ክልል ውስጥ የምትገኘውን እና በቅርብ ወራት ውስጥ ከፍተኛ ውጊያ የተደረገበትን በሰሜን ምስራቅ ቶሬስክ ሰሜናዊ ምስራቅ አካባቢ የምትገኘውን ክሪምስኬን መንደር መያዛቸውን አስታውቋል።
ከፍተኛ የሰው እና የቁሳቁስ ኪሳራ ቢደርስበትም የሩሲያ ጦር በዶኔትስክ ቀስ በቀስ እየገሰገሰ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በክልሉ የሚገኙ የዩክሬን ወታደሮች ባለፈው ማክሰኞ ፣ በጦርነቱ ላይ ስልታዊ ጠቀሜታ ባለው የወታደራዊ ማዕከል በሆኑት በቶሬስክ እና ቻሲቭ ያርበ ከተሞች አካባቢ ከፍተኛ ውጊያ መካሄዱን ተናግረዋል።
ዲፕ ስቴት የተሰኘው የዩክሬን ወታደራዊ ተንታኞች ቡድን እንዳለው የሩስያ ጦር በሁለቱ የእዝግብ ስፍራ በሆኑ ከተሞች መሃል ለወራት ቆይቷል።
በሌላ በኩል ሩሲያ በማዕከላዊ የዩክሬን ከተማ ፖልታቫ እና በሰሜን ምስራቅ ካርኪቭ ከተማ ባደረሰችው ጥቃት ቢያንስ አራት ሰዎች መገደላቸው ተገልጿል፡፡
መድረክ / ፎረም