አንድ ሕጻንና እናቱን እንዲሁም ሌሎች አራት ተሳፋሪዎችኝ የያዘ የሕክምና አውሮፕላን ፊላደልፊያ ውስጥ መኖሪያ ቤቶች ላይ ተከስክሷል።
አውሮፕላኑ ሕክምናውን ያጠናቀቀ ሕጻንና ሌሎቹን የሕክምና ተጓጓዦች ይዞ ሰሜን ምሥራቅ ፊላደልፊያ ከሚገኝ አየር ማረፊያ በተነሳ በግማሽ ደቂቃ ውስጥ ነበር የተከሰከሰው።
አውሮፕላኑ የወደቀው መኖሪያ ቤቶች አካባቢ እንደሆነም ዘገባዎች አመልክተዋል።
ተሳፋሪዎቹ በሙሉ ከሜክሲኮ የመጡ እንደሆኑም ታውቋል።
አደጋው የደረሰው ዋሽንግተን ዲስ አየር ማረፊያ 60 መንገዶኞችን ይዞ ሊያርፍ የተቃረበ አውሮፕላን ከአንድ ወታደራዊ ሄሊኮፕተር ጋራ ተጋጭቶ በተከሰከሰና ሁሉም ተሳፋሪዎች ሕይወታቸውን ባጡ በሁለተኛው ቀን ነው።
መድረክ / ፎረም