60 መንገደኞችን እና አራት የበረራ ሠራተኞችን ጭኖ ይጓዝ የነበረ የአሜሪካ አየር መንገድ አውሮፕላን፤ ሦስት ወታደሮችን ከጫነ የአሜሪካ ጦር ሄሊኮፕተር ጋራ አየር ላይ በመጋጨቱ ሁሉም ተሳፋሪዎች ህይወታቸው ማለፉ በትላንትናው ዕለት ተረጋግጧል። ባለሥልጣናቱ ትክክለኛው የአደጋው ምክንያት ምን እንደሆነ እየመረመሩ ቢሆንም፤ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ በሬገን ዋሽንግተን ብሔራዊ አየር ማረፊያ አካባቢ ለተከሰተው አደጋ ምክንያቱ "የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ብዛሃነትን መሠረት ያደረገ የሠራተኛ ቅጥር ፖሊሲ ሊሆን ይችላል" ሲሉ ተናግረዋል።
የዋይት ኃውስ ዋና ዘጋቢ ፓትሲ ዊዳኩስዋራ ያጠናቀረችው ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም