ኢትዮጵያ ውስጥ በወጣላት "ምህረት" የሚለው ስሟ የምታወቀው አሜሪካዊቷ ሜርሲ ኤሪክሰን ኢትዮጵያ ውስጥ ከ20 ዓመት በላይ ኖራለች፣ አማርኛም ትናገራለች።
ምህረት በአማራ ክልል፣ ባሕር ዳር ከተማ ውስጥ ለ20 ዓመታት የበጎ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው ግሬስ ፋውንዴሽን መስራች ስትኾን፣ ተቋሙ አሳዳጊ አልባ ሆነው ተጥለው የተገኙ ጨቅላ ህፃናትን ሰብስቦ በማሳደግ እና የቀን ሥራ እየሠሩ ኑሯቸውን ለሚገፉ እናቶች ልጆቻቸውን በመያዝ የማቆያ አገልግሎትም ይሰጣል።
ከኢትዮጵያዊ የትዳር አጋሯ ጋራ በመኾንም አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችንም ገንብተው ከ800 በላይ ልጆችን በነፃ እያስተማሩ ይገኛሉ። ከሜርሲ ኤሪክሰን ጋራ የተደረገውን ቃለ ምልልስ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም