ዛሬ ጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም መደበኛ ስብሰባውን ያካሄደው የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ተማሪዎች ከአፍ መፍቻቸው በተጨማሪ አንድ የሀገር ውስጥ ቋንቋ እንዲማሩ የሚያደርግ ዐዋጅ አጽድቋል።
ከፌደራል የሥራ ቋንቋዎች መካከል የሆነ አንድ ተጨማሪ የሀገር ውስጥ ቋንቋ ከ3ኛ ክፍል ጀምሮ እስከ 10ኛ ክፍል እንደሚሰጥ በዐዋጁ ተጠቅሷል።
ዐዋጁ፣ ከአማርኛ በተጨማሪ የተመረጡ አራት የፌደራል መንግሥት የሥራ ቋንቋዎች በሕገ መንግሥቱ እውቅና ከማግኘታቸው በፊት መውጣቱ ጥያቄ የሚያስነሳ መኾኑን የጠቀሱ አንዳንድ የፓርላማ አባላት ስጋታቸውን ገልጸዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም