በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሀማስ ተጨማሪ አራት እስራኤላውያን ታጋቾችን ዛሬ ለቀቀ 


ፎቶ፡ የታጋቾች ልውውጥ ሲደረግ የሚያሳይ በድሮን የተነሳ ምስል
ፎቶ፡ የታጋቾች ልውውጥ ሲደረግ የሚያሳይ በድሮን የተነሳ ምስል

ሃማስ በጋዛ በተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት መሰረት በሁለተኛው ዙር ልውውጥ የፍልስጤም እስረኞችን ለማስለቀቅ አራት ሴት ታጋች እስራኤላውያንን ለቀቀ፡፡

በእስራኤል የተያዙ 200 ፍልስጤማውያን እስረኞችን ለማስለቀቅ በጋዛ ከተማ ታግተው የነበሩትን አራት እስራኤላውያን ሴቶችን ለቀይ መስቀል ዛሬ አስረክቧል፡፡

አራቱ ሴቶች ካሪና አሪዬቭ፣ ዳንኤላ ጊልቦአ፣ ናአማ ሌቪ እና ሊሪ አልባግ መሆናቸውን ሃማስ ትላንት አርብ አስታውቆ ነበር፡፡

አራቱም ሴቶች የእስራኤል ወታደሮች ሲሆኑ ሀማስ ጥቃቱን በከፈተበት በደቡባዊ እስራኤል ከሚገኘው ናሃል ኦዝ ጣቢያ እአ አ በጥቅምት 7 2023 የተጠለፉ ናቸው።

አራቱ የእስራኤል ወታደሮች ከፍልስጤም አደባባይ መድረክ ላይ ሆነው በፈገግታ ታጅበው ህዝቡን እጃቸውን በማውለብለብ ሰላምታ ሲሰጡም ታይተዋል፡፡

የእስራኤል የእስር ቤት አገልግሎት 200 ፍልስጤማውያንን ለመልቀቅ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡ ከሚለቀቁት መካከልም በእስራኤል ላይ ሃማስ ባደርሰው ጥቃት ተከሰው የእድሜ ልክ እስራት የተፈረደባቸው 120 ሰዎች ይገኙበታል።

የተኩስ አቁም ስምምነት የመጀመርያ ቀን በሆነው ጥር 11 2017 ዓ.ም ፣ ሃማስ 90 የፍልስጤም እስረኞች ልውውጥ ሶስት እስራኤላዊ ታጋች ሴቶችን መልቀቁ ይታወሳል፡፡

በእስራኤልና ሃማስ መካከል ስምምነት እንዲደረስ ግብጽ፣ ኳታርና ዩናይትድ ስቴት የማሸማገል ሚናን ተወጥተዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG