በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሄግሴት በጠባብ የድምጽ ብልጫ የመከላከያ ሚንስትርነታቸው ጸደቀ 


ፋይል፡ ፒት ሄግሴት በህግ መወሰናው ምክርቤት ማብራርያ ሰጥተው ሲወጡ የተነሱት (ጥር 6፣ 2017 ዓ.ም).
ፋይል፡ ፒት ሄግሴት በህግ መወሰናው ምክርቤት ማብራርያ ሰጥተው ሲወጡ የተነሱት (ጥር 6፣ 2017 ዓ.ም).

የዩናይትድ ስቴትስ የህግ መወሰኛ ምክርቤት በዶናልድ ትራምፕ የመከላከያ ሚንስትር ተደርገው የተመረጡትን ፒት ሄግሴትን ሹመት ትላንት አርብ ምሽት 51 በ50 በሆነ ድምጽ አጽድቆላቸዋል፡፡

አንድ መቶ አባላት ያሉት ምክርቤቱ ድምጻቸውን እኩል በእኩል ሃምሳ ሃምሳ ድጋፍና ተቃውሞ የሰጡ ሲሆን የመለያ የሆነውን አንድ ድምጽ የሰጡት ምክትል ፕሬዘዳንቱ ጀ ዲ ቫንስ ናቸው፡፡

ይህም በዩናይትድ ስቴትስ ታሪክ የህግ መወሰኛው ምክርቤት መሪ የሆኑት የሀገሪቱ ምክትል ፕሬዘዳንት የመለያ ድምጽ ሰጥተው ሹመቱ መቋጫ እንዲያገኝ ሲያደርጉ ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡

ድምጽ መስጠቱ የተካሄደው በዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ከፍተኛ የሲቪል ስልጣን በሆነው የሀገሪቱን የጦር ሃይሎች በማስተዳደር ረገድ የሄግሴት ብቃትን አስመልክቶ የህግ መወሰኛ ምክርቤቱ ለቀናቶች ክርክር ሲያደርግ ከቆየ በኋላ ነው።

ሄግሴት በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በነበራቸው የምክር ቤቱ የሹመት ማረጋገጫ ማብራርያ ላይ በሀገሪቱ ወታደራዊ ሃይል ዘንድ ተጠያቂነትን እንደሚያሰፍኑ ተናግረዋል፡፡

የፎክስ ኒውስ የውይይት አቅራቢ የነበሩት ሄግሴት "ጾታዊ ጥቃት ፈጽመዋል እንዲሁም ካለመጠን ይጠጣሉ" በሚል ይወነጀላሉ፡፡

ሄግሴት ሹመታቸው የጸደቀላቸው የሃገሪቱ መከላከያ ሚንስቴር በዓለም ዙሪያ ከሶስት ሚሊየን በላይ አባላት ያሉትና በየ አመቱ 857 ቢሊየን ዶላር በጀት የሚመደብለት ተቋም ነው፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG