የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትላንት አረብ በሰደድ እሳት የተጎዳችውን ካሊፎርኒያን በጎበኙበት ወቅት የፌደራል መንግስት ሙሉ በሙሉ ከካሊፎርኒያ ጎን ይቆማል ብለዋል፡፡ እንደአስፈላጊነቱም ተመልሰው ለመጎብኘት ቃል ገብተዋል፡፡
ትራምፕ በሎስ አንጀለስ ፓስፊክ ፓሊሳዴስ ሰፈር ውስጥ በሚገኝ የእሳት አደጋ ጣቢያ ለተሰበሰቡ የአካባቢው መሪዎች “ እኔና ቀዳማዊት እመቤት በካሊፎርኒያ የተገኘነው ለካሊፎርኒያ ሰዎች ያለንን ፍቅር ለመግለጽ ነው” ሲሉ ተደምጠዋል።
ሰፈሩ በቅርብ ጊዜ በተከሰቱት የእሳት ቃጠሎዎች ክፉኛ ከተጠቁት አንዱ ሲሆን ተከታታይ ቤቶችም ወደ አመድነት ተቀይረዋል፡፡
በሎስ አንጀለስ አካባቢ ያሉ የእሳት አደጋ ተከላካዮች በከፍተኛ ንፋስ እና ደረቅ ሁኔታዎች ውስጥ በርካታ የእሳት ቃጠሎዎችን መጋፈጣቸውን እንደቀጠሉ ነው፡፡
ፕሬዘዳንት ትራምፕ በጉብኝታቸው አስቀድመው በአካባቢው በእግር ጉዞ ላይ የተሳተፉ ሲሆን በሄሊኮፕተርም በአካባቢው ያለውን የማገገም ጥረቶችን ተመልክተዋል ።
ትራምፕ ካሊፎርኒያን ከመጎበኘታቸው በፊት በሃሪኬን ሄለን የተጎዳችውን ሰሜን ካሮላይና ጎብኝተዋል ፣እዚያም ለወራት የፈጀውን የማገገሚያ ጥረቶች ዙርያ ገለፃ ተደረጎላቸዋል።
መድረክ / ፎረም