በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ የፓናማ ቦይን ለመቆጣጠር ግፊት እያደረጉ ባሉበት ሩቢዮ ወደ መካከለኛው አሜሪካ ሊያቀኑ ነው


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማርኮ ሩቢዮ
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማርኮ ሩቢዮ

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ የፓናማ ቦይን ለመቆጣጠር ግፊት እያደረጉ ባሉበት እና ዋሽንግተን ሕገ-ወጥ ስደትን ለመግታት ጥረት በያዘችበት በአሁኑ ወቅት አዲሱ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማርኮ ሩቢዮ ፓናማን እና በመካከለኛው አሜሪካ የሚገኙ ሌሎች ሃገራትን ሊጎበኙ ነው።

ጉዞው የሩቢዮ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ከሆኑ በኋላ የመጀመሪያው የውጭ አገር ጉብኝታቸው ነው። ‘ፖለቲኮ’ የተባለው የዩናይትድ ስቴትስ የዜና ወኪል እንደዘገበው የሩቢዮ ጉዞ ፓናማን፣ ጓቲማላን፣ ኤልሳልቫዶርን፣ ኮስታሪካን እና ዶሚኒካን ሪፑብሊክን ያካትታል።

በአንጻሩ ጉዳዩን አስመልክቶ የተጠየቁት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት አስተያየት “በአሁኑ ወቅት ይፋ የምናደርገው ጉዞ የለም” ሲሉ መልሰዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ፕሬዝዳንት ትረምፕ የፓናማ ቦይን በዩናይትድ ስቴትስ ቁጥጥር ስር ለማድረግ የያዙትን አላማ ለማሳካት የወታደራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እርምጃዎች አማራጭነት ውድቅ አለማድረጋቸውን ተናግረዋል።

ሩቢዮ ወደ አሜሪካ የሚገቡት ህጋዊ ሰነድ የሌላቸውን ስደተኞች ማስቆምን ጨምሮ ቅድሚያ የሚሰጧቸውን የውጭ ፖሊሲ ዕቅዶች በሳምንት መጀመሪያ ላይ ይፋ አድርገው ነበር።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG