በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደረቅ አየርና አደገኛ ነፋስ የካልፎርኒያውን ሰደድ እሳት እንዳያባብሰው ተሰግቷል


የእሳት አደጋ ሠራተኛው ሰደድ እሳቱን እያጠፋ፤ በፖዌይ ፣ ካሊፎርኒያ
የእሳት አደጋ ሠራተኛው ሰደድ እሳቱን እያጠፋ፤ በፖዌይ ፣ ካሊፎርኒያ

በካልፎርኒያ እየቀጠለ ያለው የሰደድ እሳት በአካባቢው በሚከሰተው ደረቅ አየርና አደገኛ ነፋስ አማካይነት ሊባባስ እንደሚችል ብሔራዊው የአየር ትንበያ አገልግሎት አስጠንቅቋል። ይህን ተከትሎም የእሳት አደጋ መከላከያ አገልግሎት ክፍሎች እንደ አዲስ ሊስፋፋ የሚችለውን የሰደድ እሳት ለመመከት የአደጋ ሠራተኞችን እና መሣሪያዎችን ዝግጁ አድርገዋል።

በሎስ ኤንጀለስ እና አካባቢው ላለፉት ሁለት ሳምንታት በቀጠለው አደገኛ ሰደድ እሳት ቢያንስ 27 ሰዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ፣ ሳንታ አና በመባል የሚታወቀው ነፋስ ከደረቅ የአየር ሁኔታ ጋራ ተዳምሮ እሳቱን በፍጥነት እንዳስፋፋው ታውቋል።

የሎስ ኤንጀለስ ከተማ ከንቲባ ኬረን ባስ “ሁሉም ጥንቃቄ ያድርግ” ሲሉ ጥሪ አድርገዋል።

ሁለቱ ከፍተኛ ቃጠሎዎች ማለትም በፓልሴድስ እና በኢተን የሚገኘው ሰደድ እሳት አሁንም እንደቀጠለ የግዛቲቱ የደንና እሳት አደጋ መከላከያ ቢሮ አስታውቋል። በሁለቱ ሥፍራዎች 14 ሺሕ የሚሆኑ ቤቶችና ሌሎች ንብረቶች መውደማቸውም ታውቋል።

በሌላ በኩል የካልፎርኒያው አገረ ገዥ ጋቪን ኒውሰም ደቡብ የግዛቲቱን ክፍል ከመሬት ናዳና ጎርፍ መጠበቅ የሚያስችል ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG