በምያንማር፣ በሕገ ወጥ ቡድኖች እገታ ለአስገዳጅ የገንዘብ ማጭበርበር ወንጀል ሥራ ተዳርገው የሚገኙ ዜጎች ያሉበት ሠቆቃ እንደሚያሳስባቸው የገለጹ የቤተሰብ አባላት፣ ወደ አገራቸው ለማስመለስ የኢትዮጵያ መንግሥት የላቀ ጥረት እንዲያደርግ ተማፅነዋል፡፡
ሁለት የቤተሰብ አባላት ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት አስተያየት፣ ታጋቾቹ ያሉበት ችግር እየተባባሰ እንደኾነ አመልክተዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው በበኩላቸው፣ መንግሥት ዜጎቹን ለማስለቀቅና ወደ አገራቸው ለመመለስ ጥረት በማድረግ ላይ መኾኑን ጠቅሰው፣ እስከ አሁን 41 የሚደርሱ ዜጎችን ማስመለሱን አስታውቀዋል።
ከቤተሰቦቻቸው በቀረበ መረጃ መሠረት፣ የ380 ታጋቾች ስም እና የፓስፖርት ኮፒ ጃፓን ለሚገኘው የምያንማር ኤምባሲ መሰጠቱንም ቃል አቀባዩ ገልጸዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም