በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያን የሙዚቃ ታሪክ የከተበው ደራሲ


ይነገር ጌታቸው፣ "ትዝታን በዜማ'' የተሰኘ በቀደሙት የሙዚቃ ሥራዎች ላይ ያተኮሩ ዝግጅቶች በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ኤፍኤም ዐዲስ 97.1 በሚቀርቡበት የራዲዮ ፕሮግራም ላይ አዘጋጅ ኾኖ ሠርቷል፡፡

ይኸው አጋጣሚ፣ ቆየት ካሉት የኢትዮጵያ ሙዚቃዎች ጋራ እንዲተዋወቅ ዕድሉን እንደፈጠረለት የሚገልጸው ይነገር፣ በዚኽም ታሪኩን እንዲያጠናና በመጽሐፍ ከትቦ ለአንባብያን ለማድረስ እንዲተጋ እንዳደረገው ይናገራል፡፡

በ2013 ዓ.ም. በእውቁ የሙዚቃ አቀናባሪ ኤልያስ መልካ ዜና ሕይወት እና ሥራዎች ላይ ባተኮረውና "የከተማው መናኝ" በተሰኘው የመጀመርያ መጽሐፉ ነበር ከአንባብያን ጋራ የተዋወቀው።

መጸሐፉ፥ "በቁጥር አነስተኛ ናቸው" የሚላቸው በኢትዮጵያ ሙዚቃ ላይ አሻራቸውን ማሳረፍ ከቻሉት የሙዚቃ ባለሞያዎች ውስጥ ነፍስ ኄር ኤልያስ መልካ አንዱ እንደነበር ያወሳል።

 የኢትዮጵያን የሙዚቃ ታሪክ የከተበው ደራሲ
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:05 0:00

ጸሓፊው ይነገር ከሁለት ዓመት በኋላም፣ ሚያዝያ 20 ቀን 2015 ዓ.ም. በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ላይ ያተኮረውን "ጠመንጃ እና ሙዚቃ" የተሰኘ መጽሐፉንም አስከትሎ አሳትሟል፡፡

ይህ መጽሐፍ፥ ፖለቲካን፣ ታሪክንና ሙዚቃን አሰናኝቶ የያዘ ነው፤ ይላል ደራሲው ይነገር ጌታቸው። ይህም ኾኖ፣ የኢትዮጵያ ሙዚቃ "በበቂ መጠን አልተጠናም፤ ቀጣይ ሥራዎች ያስፈልጋሉ፤" በማለት ያመለክታል፡፡

በአሁኑ ወቅትም፣ በማኅበረሰባዊ ታሪክ ላይ ያተኮረ መጽሐፍ እያዘጋጀ እንደሚገኝ የጠቆመው ይነገር፣ ሲጠናቀቅ ለአንባብያን እንደሚደርስም ተናግሯል፡፡

አስማማው አየነው፣ በእነዚኽ ሥራዎቹና ቀጣይ ሕልሞቹ ላይ ከይነገር ጌታቸው ጋራ ቆይታ አድርጓል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG