በአፋር ክልል ዐዋሽ ፈንታሌ ዶፋን ተራራ አካባቢ በተደጋጋሚ እየተከሰተ በሚገኘው ርዕደ መሬት፣ በቀጥታ የአደጋ ተጋላጭ በሚል ከተለዩ ቀበሌዎች እስከ አኹን 54 ሺሕ ሰዎች ቀዬአቸውን ለቀው እንዲወጡ መደረጉን ክልሉ አስታወቀ። በርዕደ መሬቱ ምክኒያት ለአደጋ በመጋለጣቸው አካባቢው ለቀው መውጣታቸውን የተናገሩት በአደጋው 37 ትምሕርት ቤቶች እና 13 የጤና ተቋማት መውደማቸውን የክልሉ ትምሕርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶ/ር አደም ሙሳ ተናግረዋል።
የአሜሪካ ድምጽ ዘጋቢ ገልሞ ዳዊት የመሬት መንቀጥቀጡ በተከሰተበት ማዕከል ተገኝቶ ነዋሪዎችን አነጋግሯል።
መድረክ / ፎረም