የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኒቡ ባለፈው ሳምንት በሰሜን ምሥራቅ ቦርኖ ግዛት በዳምቦዓ በሚገኝ ወታደራዊ ካምፕ ላይ ስድስት ወታደሮችን የሞቱበት የሽብር ጥቃት እንዲጥራ ትዕዛዝ ሰጥተዋል።
ፕሬዝዳንቱ ባወጡት መግለጫ የአሁኑ ምርመራ ወደፊት ሊከሰቱ የሚችሉ ሁኔታዎችን ለማስወገድ እና ያሉ የደህንነት ክፍተቶችን ለመለየት ይረዳል ብለዋል።
የፕሬዚዳንቱ መግለጫ ሐሙስ ዕለት በመረጃ አማካሪያቸው ባዮ ኦናኑጋ የተለቀቀ ሲሆን፤ በሳቢን ጊዳ በሚገኘው የዳምቦዓ ወታደራዊ ካምፕ ላይ ስለደረሰው ጥቃት አጠቃላይ ምርመራ እንዲደረግ ጠይቋል።
የናይጄሪያ ጦር በምዕራብ አፍሪካ እስላማዊ መንግሥት ታጣቂዎች በተቀነባበረ የደፈጣ ጥቃት በጎርጎርሳውያኑ ጥር 4/ 2025 ዕለት ስድስት ወታደሮችን ተገድለዋል ሲል አስታውቋል።
ባለሥልጣናት እንዳሉት ምርመራው ለችግሩ መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ የመረጃ ክፍተቶችን እና የአሰራር ቅልጥፍናን ጉድለትን በመለየት ላይ ያተኩራል።
ፕሬዝዳንቱ በጥቃቱ ወቅት የጸጥታ ሃይሎች በተለይም የአየር ክፍሉ ያደረገውን ፈጣን ጣልቃ ገብነትን አድንቀዋል።
መድረክ / ፎረም