በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ በኦሮሞ ነፃነት ታጣቂዎች ተፈፀመ በተባለ ጥቃት ሁለት ሰዎች ትላንት መገደላቸውን ነዋሪዎችና ቤተሰቦቻቸው ለአሜሪካ ድምፅ አስታወቁ።
የኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ ሰላም እና ፀጥታ ጽሕፈት ቤት፣ ከብቶቻቸውን ሲጠብቁ ነበሩ ያላቸው ሁለት ሲቪሎች ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ወሰን የተሻገቱ ባሏቸው ታጣቂዎች መገደላቸውን አስታውቋል።
በግድያው ስሙ ተነስቶ የተወነጀለው የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ቃለአቀባይ አቶ ጅረኛ ጉዴታ፣ ታጣቂዎቻቸ ጥቃት አለማድረሳቸውን ገልጸው አስተባብለዋል።
መድረክ / ፎረም