በበርካታ የአሜሪካ ግዛቶች ከትላንት ዕሁድ ጀምሮ የጣለው በረዶና ኅይለኛ ነፋስ ትምህርት ቤቶችና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እንዲዘጉ አስገድዷል።
በመካከለኛው፣ በደቡብ እና በምሥራቅ የሃገሪቱ ክፍሎች በመጣል ላይ ያለው በረዶ በተለይም በአንዳንድ ሥፍራዎች በአሥርት ዓመታት ያልታየ መጠን ሊሆን እንደሚችል በመነገር ላይ ነው።
የአሜሪካ ድምጽ የሚገኝበት ዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢዋ ያሉ ግዛቶች በበረዶ የተሸፈኑ ሲሆን፣ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና ትምሕርት ቤቶች ዝግ ሆነዋል። በሥራ ገበታቸው ላይ የግድ መገኘት ያለባቸው ሠራተኞች ግን በአስቸጋሪው በረዶ በእግር፣ በባቡር እና በአውቶቡስ ተጉዘው ሥራቸው ላይ ለመገኘት ችለዋል።
በረዶው ሲጥል ውሎ እንደሚያመሽ የአየር ትንበያ ሲያመለክት፣ እጅግ ቃዝቃዛው የሆነው አየር ቀጣዮቹን ቀናት አስቸጋሪ እንደሚያደርግ ተሰግቷል።
መድረክ / ፎረም