በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የካናዳው ጠቅላይ ሚንስትር ከፓርቲያቸው መሪነት ለቀቁ


የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ታህሳስ 28/2017
የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ታህሳስ 28/2017

የካናዳው ጠቅላይ ሚንስትር ጀስቲን ትሩዶ ከለዘብተኛው ፓርቲ መሪነት ራሳቸውን ማግለላቸውን ዛሬ አስታውቀዋል።

በአመራራቸው ላይ ተቃውሞ የበረታባቸው ትሩዶ በተለይም የገንዘብ ሚንስትራቸው ከሥልጣናቸው መልቀቃቸው በመንግሥታቸው ውስጥ ያለው ችግር የበረታ መሆኑን አመላክቶ ነበር።

በፓርቲያቸው ውስጥ ያለው መፋተግ የሚያመለክተው በመጪው ምርጫ ለመሳተፍ እርሳቸው ጥሩ አማራጭ አለመሆናቸውን እንደሆነ ትሩዶ ተናግረዋል።

ፓርቲው አዲስ መሪ እስከሚመርጥም በጠቅላይ ሚንስትርነት እንደሚቆዩ ትሩዶ አስታውቀዋል።

ከሃያ ቀናት በኋላ ሥራውን መልሶ እንደሚጀምር ይጠበቅ የነበረው ፓርላማም እስከ መጋቢት አጋማሽ ድረስ እንደማይመለስ ተነግሯል። ባለው ጊዜም ለዘብተኛ ፓርቲው መሪውን እንደሚመርጥ ይጠበቃል።

በካናዳ ሦስቱም ዋና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ፓርላማው በሚከፈትበት ወቅት ለዘብተኛ ፓርቲውን የትምምን ድምጽ ነፍገው ከሥልጣን እንደሚያስወግዱ አስታውቀው ነበር።

ጀስቲን ትሩዶ ወደ ሥልጣን የመጡት ከአስር ዓመታት በፊት እ፡አ፡አ በ2015 ነበር። ይህም ለ10 ዓመታት የወግ አጥባቂ ፓርቲው ሃገሪቱ ከመራ በኋላ መሆኑ ነው።

የምግብ ሸቀጥ ዋጋ እና የመኖሪያ ቤት መወደድ እንዲሁም የስደተኞች ቁጥር መጨመር ድምጽ ሰጪዎች በትሩዶ ላይ እንዲያማርሩ ምክንያት እንደሆነ ተነግሯል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG