በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ


አንጋፋ ፖለቲከኛ እና የንግድ ሰው አቶ ቡልቻ ደመቅሳ
አንጋፋ ፖለቲከኛ እና የንግድ ሰው አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ኢትዮጵያዊው አንጋፋ ፖለቲከኛ እና የንግድ ሰው አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በ94 ዓመታቸው ዛሬ ታኅሣሥ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታየቸውን የአሜሪካ ድምፅ ከቤተሰባቸው መረዳት ችሏል።

አቶ ቡልቻ ከ1995 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ፖለቲካ በግንባር ቀደምትነት ከሚሳተፉ የፖለቲካ ሰዎች አንዱ ነበሩ።

አቶ ቡልቻ የተቃዋሚው የኦሮሞ ፌደራሊስት ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ መስራቾች አንዱ ሲኾኑ፣ በአንድ ወቅት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልም ነበሩ።

ከ1990ዎቹ ጀምሮ በሰላማዊ የተቃውሞ ፖለቲካ ውስጥ ሲሳተፉ ቆይተዋል።

አቶ ቡልቻ በ1967 ዓ.ም በፋይናንስ ምክትል ሚኒስትርነት፣ ሀገራቸውን ወክለውም በዓለም ባንክ ቦርድ አባልነት አገልግለዋል።

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ምኒስትር ዐብይ አህመድ በአቶ ቡልቻ ደመቅሳ ህልፈት የተሰማቸውን ሐዘን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አጋርተዋል።

ጠቅላት ሚኒስትሩ አቶ ቡልቻ “በሚችሉት ሁሉ ሀገራቸውንና አፍሪካን ያገለገሉ፣ በአቋማቸው ጽኑ፣ ሕዝቦችን ለማቀራረብ የተጉ፣ እውነት ነው ብለው ያመኑትን የትምና መቼም የሚናገሩ” ነበሩ ብለዋል። የአቶ ቡልቻ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ፕሮግራም ልጆቻቸው ከሚኖሩበት አሜሪካ ኢትዮጵያ ከደረሱ በኋላ እንደሚወሰንም ከቤተሰብ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG